ታኅሳስ 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአዘርባጃን ፕሬዝዳንት አውሮፕላኑ በሩሲያ በጥይት ተመትቷል ሲሉ ለሞስኮ ሶስት ጥያቄዎችን አቅርበዋል። የአዘርባጃን ፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭ ትላንት ሞስኮን ተችተው ባሳለፍነው ሳምንት የተከሰከሰው የአዘርባጃን አውሮፕላን በሩሲያ ጥቃት ደርሶበታል ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ ለአዘርባጃን ስቴት ቴሌቪዥን እንደተናገሩት “አውሮፕላኑ በሩሲያ በጥይት መመታቱን ሙሉ በሙሉ ግልጽ አድርገን መናገር እንችላለን ነገር ግን ግልጽ ማድረግ የምንፈልገዉ ሆን ተብሎ ነው የተደረገው እያልን አለመሆኑን ነዉ ብለዋል።
አሊዬቭ ሩሲያን ለብዙ ቀናት ጉዳዩን ለማፈን በመሞከር ወቅሰዋል። በመጀመሪያዎቹ ሶስት ቀናት ውስጥ ከሩሲያ ምንም ነገር አልሰማንም ብለዋል ።
የአዘርባጃን አውሮፕላን በካዛክስታን ተከስክሶ 38 ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን በግሮዝኒ አቅራቢያ ለማረፍ ሲሞክር እንደነበር ይታወቃል ።
ቅዳሜ እለት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የአዘርባጃኑን ፕሬዝዳንት እና ክሬምሊንን ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ የአየር መከላከያ ስርዓታቸው በግሮዝኒ አቅራቢያ በዩክሬን ሰው አልባ ጥቃት ላይ መተኮሱን ተናግረዋል። በአደጋው ጉዳይ አዘርባጃን ለሩሲያ ሦስት ጥያቄዎችን እንዳቀረበች አሊዬቭ ተናግረዋል።
በመጀመሪያ ሩሲያ አዘርባጃንን ይቅርታ መጠየቅ እንዳለባት፣ ጥፋቱን ሞስኮ ማመን እንደሚገባት፣ ሶስተኛ ጥፋተኛውን መቅጣት እና ለአዘርባጃን ግዛት፣ ለተጎዱት ተሳፋሪዎች እና የበረራ አባላት ካሳ መክፈል እንዳለባት የሚጠይቅ ነዉ ብለዋል ።
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ እሁድ እለት ለሩሲያ መንግስት ሚዲያ እንደተናገሩት ተጨማሪ ዝርዝሮችን ሳይሰጡ ፑቲን በድጋሚ አሊዬቭን በስልክ አነጋግረዋል ብለዋል ።
በሌላ በኩል በሩሲያ፣ አዘርባጃን እና ካዛኪስታን የጋራ ምርመራ በአክታው ከተማ በአደጋው ቦታ ላይ ተጀምሯል ሲል ዘ ዊክ ዘግቧል ።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ