ታኅሳስ 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የተፈናቃዮች ሃሳብ እንዲደመጥ አካታች አጀንዳ የማሰባሰብ ኃላፊነት እንዳለበት ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
እስካሁን በ971ዱም ወረዳዎች በተካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰበብ ስራ ተፈናቃዮችን ያሳተፈ ውይይት መደረጉን የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ለጣቢያችን ገልጸዋል።
በተለያዩ ምክንያቶች በሒደቱ ያልተሳተፉ አንዳንዶች አጀንዳቸውን ለኮሚሽኑ ልከው የታየላቸው እንዳሉም ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።
ኮሚሽኑ ተፈናቃዮችን ወደ መደበኛ ቀያቸው የመመለስ ስልጣን ባይኖረውም፤ የሚፈናቀሉበትን ምክንያት የማስቆምና እንደ ህዝብ ተፈናቃዮችንም የማወያየት፤ አጀንዳም የመሰብሰብ ግዴታና ሃላፊነት እንዳለበት ተናግረዋል።
በቀጣይ ኮሚሽኑ በትግራይ እና አማራ ክልሎች በሚኖረው የአጀንዳ ማሰባሰብ የውይይት መድረክ ተፈናቃዮችን ማሳተፍ እና ከእነርሱም አጀንዳ መሰብሰብ ቁልፍ የሂደቱ አካል መሆኑን ፕሮፌሰር መስፍን አስታውቀዋል።
በተለይ ቀጣይ የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራ በሚከናወንባቸው የአማራና ትግራይ ክልሎች በርካታ ተፈናቃዮች እንደሚኖሩ በማሰብ ኮሚሽኑ ከወዲሁ ዝግጅት ማድረጉን ለጣቢያችን ተናግረዋል።
ቀሪ የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራ የሚከናወንባቸው የትግራይ እና አማራ ክልሎች በርካታ ተፈናቃይ እንደሚኖርባቸው የሚገመት በመሆኑ ኮሚሽኑ ሁሉንም ለማሳተፍ ጥረት እንደሚያደርግ የገለጹት ዋና ኮሚሽነሩ፤ ሀገራዊ ምክክሩ ከጅምሩም ያስፈለገው ሰዎች ሳይፈናቀሉ በሀገራቸው በሰላም እንዲኖሩ ለማስቻል ነው ብለዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ