ታኅሳስ 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)39ኛው የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተር በ100 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 2022 የዓለም የሰላም ኖቤል ተሸላሚው እና በአሜሪካ ታሪክ እረጅሙን ዕድሜ በሕይዎት የኖሩት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተር በጆርጂያ ግዛት በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ህይወታቸው ማለፉን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
የጂሚ ካርተርን ሕልፈት ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና አዲሱ የአሜሪካ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናንድ ትራምፕን ጨምሮ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ሀዘናቸውን እየገለፁ ናቸው፡፡
1924 የተወለዱት ጂሚ ካርተር 4 ልጆች፣ 11 የልጅ ልጆች እና 14 የልጅ ልጅ ልጆችን ማየት ችለዋል ነው የተባለው፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ