ታኅሳስ 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ የአውቶቢስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከሚሰጡ መስመሮች 19ኙ በቋሚነት እስከ ምሽት 4፡00 ሰዓት አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን የከተማው የአውቶቢስ ድርጅት ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
ከ1 ወር በፊት በከተማዋ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት አገልግሎት ውስንነት ለመቅረፍ፣ እንዲሁም ምሽት ላይ ነዋሪዎች የሚያጋጥማቸውን የትራንስፖርት ችግር ለማቅለል፣ የአገልግሎት አሰጣጡ እስከ ምሽት 4 ሰዓት እንዲራዘም መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አዉቶቡስ ድርጅት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
በ5 ቅርንጫፎች የስምሪት ሂደቱን እየተቆጣጠሩ መሆኑን የሚገልጹት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቢስ ድርጅት የኢንተለጀንስ ትራንስፖርት ሲስተምና ኦፕሬሽን አገልግሎት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰብስባቸዉ መንግስቴ፣ በከተማዋ ካሉት መስመሮች 19ኙ እስከ ምሽት 4 ሰዓት በቋሚነት አገልግሎቱን እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለጊዜው የአገልግሎት ፈላጊዎች ቁጥር እና ሰልፍ የሚበዛባቸው አከባቢዎች ተልይተው ቅድሚያ ተሰጥቷቸው፣ እስከ ምሽት 4፡00 ሰዓት አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን የተናገሩት አቶ ሰብስባቸው፣ በቀጣይ ሁሉም መስመሮች በቋሚነት እስከ ምሽት 4፡00 ሰዓት አገልግሎት እንዲሰጡ እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡
አሁን ላይ ምሽት ከ3 እስከ 4 ሰዓት አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉ ጅምር እንደሆነ ገልጸው፣ በቀጣይ ከዚያም በላይ አምሽተውና በጊዜ ሂደት ደግሞ የ24 ሰዓት አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ እንደሚሰራ አመላክተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከቀናት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው 4ተኛ ዓመት፣ 4ተኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በከተማዋ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት እስከ ምሽቱ 4:00 የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ መወሰኑ የሚታወቅ ነው፡፡
በዚህም ማንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አውቶቡሶች፣ ሚዲ ባስ እና ሚኒ ባሶች፣ ቢሮው ባወጣው መደበኛ ቀን በሚሰሩበት መስመር እና ቀን ላይ በሚከፈለው ህጋዊ ታሪፍ መሠረት እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት አገልግሎት እንዲሰጡ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ማስታወቁም አይዘነጋም።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ