ታኅሳስ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዚህ ባለንበት ወርሃ ታህሳስ መጨረሻ ላይ የሚከበረዉን የገና በዓል በስፋት ከሚከበርባቸው ቦታዎች መካከል አንዱ የላሊበላ ከተማ እንደሆነ ይታወቋል፡፡የገና በዓልን ተከትሎ 1.5 ሚሊየን የሚጠጉ ጎብኚዎች ወደ ከተማዋ ይመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የላሊበላ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታዉቋል፡፡
የላሊበላ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ወንድምነው ወዳጆ ከተማዋ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራ ብትሆንም ባለፉት ጊዜያት በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተዉ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና እንደ ሀገር ያሉ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታዎችን ተከትሎ ይገኛል ተብሎ የሚታሰበዉ ገቢ መቀነሱን አስረድተዋል፡፡
ይህን ለማካካስ አሁን ከፊታችን የሚከበረዉን የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ገናን በደመቀ ሁኔታ በታሪካዊቷ ላሊበላ ከተማ ለማክበር እና እንግዶችን ለማስተናገድ ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸዉን ተናግረዋል፡፡በዚህ ከ1.5 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ዜጎች ወደ ከተማዋ በዓሉን ለማክበር ይመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ያስረዱት ምክትል ከንቲባው፤በቂ የሆነ የሆቴል እንዲሁም የበይነ መረብ አገልግሎት መስጠት እንዲቻል የሚያደርጉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን አመላክተዋል፡፡
አያይዘውም በከተማዋ አንጻራዊ የሆነ የሰላም ሁኔታ በመኖሩ ጎብኚዎች ያለምንም ስጋት ስፍራውን መጎብኘት እና ክብረ -በዓሉንም መታደም እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡ አክለዉም የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ቅርስ ላይ እየተደረጉ ያሉ ጥገናዎች መኖራቸውን አንስተው፤ዘላቂ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራ ለማድረግ በቂ የመሰረተ -ልማት ስራዎች እየተሰሩ እንዳሉም ጠቁመዋል፡፡
የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ኢትዮጵያ የነበራትን ድንቅ የኪነ-ህንጻ ጥበብ ማሳያ እና አሻራ መሆኑና ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ካስመዘገበቻቸዉ ቅርሶች መካከል ቀዳሚዉ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ