ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የንግድ ኢንስፔክሽን እና ሬጉላቶሪ ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ አሰፋ ለጣቢያችን እንደገለጹት ባለፉት 5 ወራት ውስጥ 1ሺ 700 ከሚሆኑ የግል እና ከ26 በላይ በሆኑ እንደ ሸገር እና ብርሃን ያሉ የመንግስት ዳቦ ቤቶች ላይ በተደረገው ክትትል 153 የሚደርሱ ከግራም በታች ለንግድ በሚያቀርቡ ዳቦ ቤቶች ላይ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በጽሁፍ እና በቃል እንደተሰጣቸው አስታውቀዋል፡፡
ማስጠንቀቂያውን የተላለፉና በድጋሚ ጥፋት የተገኘባቸው 53 የሚሆኑ የንግድ ቤቶች የማሸግ እርምጃ እንደተወሰደባቸውም አስታውቀዋል፡፡
በከተማዋ 1 ሺህ 323 የግል ዳቦ ቤቶች መኖራቸውን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ አሁን ላይ ከተፈቀደው ግራም በታች የሚሸጡትን እየተቆጣጠሩ መሆኑን እና በመሸጫ ሱቆች ላይ የግራም መጠን እንዲለጥፉ አድርገናል ብለዋል፡፡
አሁን ላይ በቁጥጥር ሂደቱ ተግዳሮት የሆነው በአዋጅ ከተቀመጠው ግራም በታች የሆኑ ምርቶችን በምሽት እና በእረፍት ጊዜያት እያመረቱ የሚሸጡ መበራከታቸው ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ የምርት አቅርቦት ማነስ ብሎም የነጻ ገበያው ነጋዴው በፈለገው ዋጋ እንዲሸጥ ማድረጉም የቁጥጥር ሂደቱን ውጤታማ እንዳይሆን አድርጎታል ሲሉ አስረድተዋል።
ሸማቹ ህብረተሰብ ከተፈቀደው ግራም በታች የሚሸጡ ነጋዴዎችን በ8588 የነጻ የሰልክ መስመር በመደወል ጥቆማ ቢሰጡ፤ ለቁጥጥር ስራው በግብዓትነት እንደሚያግዝ ገልጸዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ