👉እንዲሁም ሌላ ተከሳሽ 3 ዓመት ከ 6 ወር በሆናት ህጻን ላይ የመድፈር ሙከራ ያደረገው ወጣት በጽኑ እስራት መቀጣቱን የጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል
ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በጌዴኦ ዞን ወናጎ ከተማ አስተዳደር በ 5 ዓመት ህፃን ልጅ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች በ 19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድቤቱ ወሰነ ።
ወንጀሉ የተፈፀመው በወናጎ ከተማ አስተዳደር ቱቱፈላ ቀበሌ ኦዶላ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ሲሆን ተበዳይ የ5 ዓመት ህፃን ህዳር 14/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ዳቦ ለመግዛት በሄደችበት በሁለት ዳቦ ቤት ሰራተኞች መደፈሯን ክሱ የደረሰው የወናጎ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በቀረቡ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል።
በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ክስ የቀረበባቸው ወንጀለኞች ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ሁለቱም ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ 19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል::
ፍርድቤቱ በተጨማሪ በተመሳሳይ ቀን በዋለው ችሎት ተከሳሽ ወጣት ኤርምያስ ፀጋዬ 3 ዓመት ከ 6 ወር በሆነችው ተበዳይ ህፃን ከምትጫወትበት ቦታ ወደ ኤት ኤል ትምህርት ቤት ይዞ በመሄድ የመድፈር ሙከራ ማድረጉን በምስክር ያረጋገጠው ፍርድቤት በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ