♻️ቆጣሪዎች ሲቀየሩ ደንበኞች ምንም አይነት ክፍያ አይከፍሉም ተብሏል
👉ለፕሮጀክቱ ትግበራ ከ48 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ ይደረጋል ተብሏል
ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ካሉበት ሆነው የኤሌክትሪክ ሃይል መግዛት የሚችሉበትን የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል ፕሮጀክት ነድፎ ነባር ቆጣሪዎችን በኤስ.ቲ.ኤስ ስማርት ሜትር በመቀየር ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
ፕሮጀክቱ በሁለት ምዕራፍ የሚተገበር ሲሆን በመጀመሪያው ዙር 25 ሺህ ነባር ቆጣሪዎችን በአዲስ አበባ ለመቀየር ታቅዶ እስካሁን በባልደራስ ኮንዶሚኒየም እና በመካኒሳ ባቱ አንድ ኮንዶሚኒየም ከ1 ሺህ 6 መቶ በላይ ነባር ቆጣሪዎች በኤስ.ቲ.ኤስ ስማርት ቆጣሪዎችን መቀየር መቻሉ ተመላክቷል፡፡
በቀጣይ 3 ወራትም 10 ሺህ ነባር ቆጣሪዎችን ለመቀየር ታቅዶ እየተሠራ ነው ተብሏል፡፡
እየተቀየሩ የሚገኙት የኤስ.ቲ.ኤስ ስማርት ቆጣሪዎች ደንበኞች ወደ ማዕከል መምጣት ሳይጠበቅባቸው ካሉበት ቦታ ሆነው በእጅ ስልካቸው በመጠቀም ብቻ ኃይል መግዛት እንዲሁም የኃይል አጠቃቀማቸውን መከታተል የሚያስችሉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም የኤስ.ቲ.ኤስ ስማርት ቆጣሪዎች ደንበኞች ኃይል ገዝቶ ለመጠቀም የሚያጠፉትን ጊዜና ጉልበት ለመቀነስ ብሎም ከቢል ጋር በተያያዘ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት የሚያግዙ ይሆናሉ ነው የተባለው፡፡
በፕሮጀክቱ ሁለተኛ ዙር ትግበራ 125 ሺሕ ነባር ባለ ሶስት ፌዝ ቆጣሪዎች በመላ ሃገሪቱ ለሚገኙ ደንበኞች በአዲስ ኤስ.ቲ.ኤስ ስማርት ቆጣሪዎች የሚቀየሩ ይሆናል ተብሏል፡፡
በአጠቃላይ በዚህ ፕሮጀክት የ500 ሺህ ደንበኞች ነባር ቆጣሪዎች የሚቀየሩ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የቆጣሪዎቹ ግዢ ተፈጽሞ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ ተመላክቷል፡፡
ለፕሮጀክቱ ትግበራ ከ48 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ የሚደረግ ሲሆን ወጪው በዓለም ባንክ የሚሸፈን ነው ተብሏል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ