ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከሰሞኑ በሰጡት መግለጫ የዩኒቨርሲቲዎች በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ የሚመደብ ይሆናል ማለታቸውን ተከትሎ መናኸሪያ ሬዲዮ ውሳኔው በትምህርት ዘርፉ ላይ የሚኖረውን አሉታዊ እና አዎንታዊ ተጽዕኖ በተመለከተ ባለሙያዎችን አነጋግሯል።
የትምህርት ባለሙያው ዶ/ር አለማየሁ ከበደ እንደገለጹት፤ የዩኒቨርሲቲዎቹ በጀት የሚወሰነው በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል እንጂ የትምህርት ሚኒስቴር የበጀት ጉዳይ እንደሚመለከተው በህግም ሆነ በአዋጅ የተቀመጠ ነገር የለም ብለዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲዎቹ በመማር ማስተማር፤ በጥናት እና ምርምር ብሎም ለሀገርም ችግር ፈቺ ስራ ከመስራታቸው አንጻር የሚመደብላቸው በጀት ባመጡት ውጤት መሰረት ነው መባሉ ገልጽ አይደለም የሚሉት ባለሙያው፤ ስምምነቱ ወደ ተግባር ቢገባ በትምህርት ዘርፉ ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ ከመፈተሸ በፊት የትምህርት ሚኒስቴር በጀት የመመደብ ስልጣን እንዳለው መታወቅ አለበት ይላሉ።
ሌላኛው የትምህርት ባለሙያው ዶክተር መክብብ ጣሰው በበኩላቸው በጀትን መሰረት አደርጎ መመደብ የሚገባው የትምህርት አሰጣጥ ጥራት እና ውጤት ላይ መሰረት በማድረግ ሳይሆን ዩኒቨርሲቲዎቹ በሚኖራቸው የተማሪ መጠን እና በሚሰጡት የትምህርት ብዛት መሆን አለበት ሲሉ ገልጸው፡፡
ከዛ ይልቅ የትምህርት አሰጣጥ ጥራቱ እንዲሻሻል የተለያዩ መስፈርቶችን በማውጣት በሌላ አሰራር ቢገመገሙ የተሻለ ይሆናል የሚሉት ባለሙያው፤ አወዳዳሪ መስፈርቶችን በመጠቀም በሚያመጡት የተሻለ ውጤት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ መፍጠር የተሻለ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በጀትን መሰረት ያደረገ አሰራር ግን የመማር ማስተማር ሂደቱን በተለየም ጥራቱን ችግር ውስጥ የሚከት በመሆኑ ጥንቃቄ ያስፈልጋልም ይላሉ።
የዩኒቨርሲቲዎች በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ መመደቡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በመሰረታዊነት ለመቀየርና የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ ወሳኝ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ መናገራቸው የሚታወቅ ነው።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ