ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህፃናትም ሆነ የአዋቂዎች የልብ ህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎች እና ህክምናው ባለመኖሩ ታማሚዎች እንግልት በተሞላበት ሁኔታ ወደ አዲስ አበባ እየተላኩ እንዲታከሙ እንደሚደረግ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የልብ ህክምና ክፍል ዋና ሃላፊው ዶክተር መኳንንት መለሰ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቀዋል፡፡
ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሉ ምንም እንኳን በህክምናው ዘርፍ ቀዳሚ ቢሆንም በልብ ቀዶ ህክምና የትምህርት ዘርፍ ተማሪዎችን እንደማያሰለጥን፤ ይህ መሆኑ ደግሞ ለክልሉም ሆነ በአከባቢው ላሉ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሳለጠ የህክምና አገልግሎት እንዳያገኙ አድርጎታል ሲሉ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
በጎንደር ከተማ ባለው ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህክምናው እንዲጀመር በዘርፉ ባለሙያዎች በኩል ጥረት እየተደረግ መሆኑን አመላክተው፤ አሁን ላይ በሆስፒታሉም ሆነ በከተማው፤ አንድ ሰብ ስፔሻሊስት ዶክተር በቅርቡ የቀዶ ጥገና ስራውን ባይሰሩም መለስተኛ አገልግሎት እየሰጡ እንዳሉ ገልጸዋል፡፡
በክልሉ ለህጻናትም ሆነ አዋቂዎች የልብ ቀዶ ህክምና አገልግሎት እየተሰጠ ባለመሆኑ ታማሚውን ወደ አዲስ አበባ ለመላክ ወረፋ ስለሚኖር ከፍተኛ ተግዳሮት እየተፈጠረ መሆኑን ዶክተር መኳንንት ገልጸዋል፡፡ በቂ የህክምና አገልግሎት ባለመሰጠቱም የህጻናትን ህይወት ለማዳን ፈታኝ እንደሆነና በክልሉ አሁን ላይ ካለው የሰላም እጦት ጋር ተዳምሮ አስቸጋሪ እንዳደረገው አክለው ገልጸዋል፡፡
የጎንደር ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተሟላ የልብ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ከመንግስት በኩል የግንባታ ቦታ ማመቻቸት፤ ባለሙያዎችን መቅጠርና ገንዘብ መመደብ እንዲሁም ከተለያዩ ረጂ ድርጀቶች ሃብት ማሰባሰብ እንደሚጠበቅ ዶክተር መኳንንት ገልጸዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ