ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በታክስ ስወራ፣ የተጨማሪ ታክስ አለመክፈል፣ በኮንቶሮባንድ እና በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘውን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀል የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር ምርመራ ሲያጣራ ቆይቶ ክስ መስርቶባቸዋል።
ግለሰቦቹ የተከሰሱት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1)(ሀ)(ለ)፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ አዋጅ 285/94፣ የፌዴራል የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 116(2)፣ 125(1) እና 132 እንዲሁም ሽብርተኝነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 29(1)(ሀ)(ለ)(ሐ) እና አንቀጽ 2(መ)(ሠ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ተከሳሽ የዌብ ስፕሪክስ አይቲ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ብርሃኑ አምባዬ 51 ሚሊየን 892 ሺህ 321 ብር የንግድ ትርፍ ፍሬ የታክስ ስወራ ወንጀል በመፈጸም በ2010 ዓ.ም ባለአክስዮን በመሆን በትርፍ ክፍፍል ወቅት 1 መቶ 49 ሺህ 56 ብር ከ73 ሳንቲም ፣ በ2011 ዓ.ም ብር 52 ሚሊየን 2 መቶ 48 ሺህ፣ በ2012 ዓ.ም ብር 593 ሺህ 174 ብር ከ19 ሳንቲም የትርፍ ተካፋይ በመሆን ጥቅም ያገኘ፣ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆኖ ድርጅቱን እየመራ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ያልተፈፀመባቸውን ሶፍትዌሮች ከውጭ ድርጅቶች ጋር የግዥ ውል በመፈረም ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ጥቅም ላይ እንዲውሉ በማድረግ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ተከሳሽ አቶ መቅደስ አክሊሉ ተመስገን ሽብርተኝነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 29(1) (ሀ) (ለ)(ሐ) እና አንቀጽ 2(መ) (ሠ) ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ ሽብርተኝነትን በገንዘብ በመርዳትና በታክስ ስወራ ወንጀሎች ምክንያት የተገኘውን ገንዘብ ምንጩ እንዲደበቅና ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ባለአክሲዮን እና የቦርድ ሰብሳቢ ሆኖ በትርፍ ክፍፍል ወቅት በ2014 ዓ.ም የደረሰውን ብር 2 ሚሊየን 552 ሺህ 279 ብር ከ47 ሳንቲም በድርጅቱ ውስጥ ያለውን የአክስዮን ድርሻ በማሳደግ እና በ2015 ዓ.ም የደረሰውን 43 ሺህ 110 ብር ከ 90 ሳንቲም ለግል ጥቅሙ በማዋል ክስ የተመሰረተበት መሆኑ ታውቋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ