ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሌባ ተቀባዮች ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰረቁ የመኪና ዕቃዎችን በማከማቸት ዕቃዎቹን ለማስመለስ ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠየቅባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ ተደጋግሞ ይገለፃል።
በልደታ ክ/ተማ ፖሊስ መምሪያ የጎማ ቁጠባ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያም የተሰረቁ የተሽከርካሪ ዕቃዎችን በመኖሪያ ቤት ውስጥ በመደበቅና የተሽከርካሪዎቹ ባለቤቶች ሲመጡም የራሳቸውን ዕቃ በገንዘብ የሚሸጡ ግለሰቦች ላይ ጥናት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል፡፡
ይህን መነሻ ባደረገ እንቅስቃሴ የመኪና ዕቃዎች ላይ የሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶችን መቀነስ ላይ ያተኮረ በጥናት ላይ የተመሠረተ ህግ የማስከበር ሥራን ፖሊስ ትኩረት ሰጥቶም እየሰራ ይገኛል፡፡
ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ/ም በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ቀጠና አራት አካባቢም የቀጠናውን ኦፊሰር ተሳታፊ ያደረገ ጥናትና ኦፕሬሽን በማድረግ በተለዩ አራት የመኖሪያ ቤቶች ውስጥ ከሌቦች እየተቀበሉ በመደበቅ የሚሸጡ ግለሰቦችን በማጥናት በተደረገ ኦፕሬሽን 152 የተለያዩ ስፖኬዎች፣ 08 ዓርማዎች ( ማርክ )፣ 08 የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀር ክዳኖች፣ 01 የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀር፣ 15 የስፖኪዮ ማቀፊያ፣ 01 የሞተር ሳይክል ፍሬቻ ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡
ተመሳሳይ ወንጀል ተፈጽሞብኛል የሚል ካለ ጎማ ቁጠባ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በአካል በመቅረብ የተሠረቀበትን ዕቃ መለየትና መረከብ እንደሚችል ፖሊስ አስታውቆ ህብረተሰቡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳየ የመጣው ወንጀልን የመጥላትና ተጠርጣሪዎችን ወደ ህግ የማቅረብ ሂደት እጅግ የሚመሰገን በመሆኑ በቀጣይም ለፀጥታ ስራው እያሳየ ያለውን አጋርነት አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ