ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የደቡብ እስያ ሃገርን ለሁለት ጊዜ የመሩት እና ቀደም ሲል የገንዘብ ሚኒስትር ሆነው የህንድን ኢኮኖሚዋን ነፃ ያደረጉት የቀድሞ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማንሞሃን ሲንግ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸዉን አልጀዚራ ዘግቧል።
የማዕከላዊ ባንክ ገዥ በመሆን ያገለገሉት ኢኮኖሚስት-ፖለቲከኛ ሲንግ ታመዉ እንደነበርና በትላንትናዉ ዕለት በኒው ዴሊ በሚገኘው የህንድ የህክምና ሳይንስ ተቋም መግባታቸዉ ታዉቋል።
ሆስፒታሉ በሰጠው መግለጫ ህመማቸዉ ከቤት እንደጀመረና እራሳቸዉንም ስተዉ እንደነበር አስታዉቋል።
መግለጫው አክሎም ከእድሜ ጋር በተያያዙ የጤና እክሎች ህክምና እየተደረገላቸዉ እንደነበር ጠቅሷል።
ለ10 አመታት የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትሮች አንዱ በመሆን በታማኝ ህንዳዊያንን ማገልገላቸዉ ተገልጿል።
ህንድ ከታዋቂ መሪዎቿ አንዱ የሆኑት ዶ/ር ማንሞሃን ሲንግ ጂ በማጣቷ ሀዘን ላይ ነች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ተናግረዋል።
የምጣኔ ሀብት ምሁር ፖለቲከኛ ጉምቱ ሰዉ ነበሩ ሲሉም አወድሰዋቸዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ