ታኅሳስ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመጀመሪያ ዙር ከመስከረም 27 እስከ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ቁጥራቸው 691 ሺህ 307 የሚሆኑ ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት መከተባቸው የሚታወስ ሲሆን ከታህሳስ 3 እስከ ታህሳስ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በቆየው የሁለተኛው ዙር ክትባት ዘመቻ ከ700 ሺህ በላይ ህፃናት መከተባቸዉን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታዉቋል፡፡
በሁለተኛ ዙር ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ከ692 ሺ በላይ ሕጻናትን ለመከተብ ዕቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም 742ሺህ 467 ህፃትን መከተብ እንደተቻለ የቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ዳምጠው ተናግረዋል፡፡
ከተለያዩ ክልሎች የመጡ እና በጎዳ ላይ የሚኖሩ 2መቶ 85 ህፃናት መደበኛ ክትባትን በቋሚነት እንዲያገኙ ማድረግ መቻሉንም ገልፀዋል፡፡
በማህበረሰቡ በኩል ባለዉ የተሳሳተ ግንዛቤ ምክንያት የቀናት እና የወራት እድሜ ያላቸውን ህፃናት ለማስከተብ ወላጆች ፍቃደኛ እንዳልነበሩ የሚናገሩት ዳይሬክተሩ በእቅዳቸው መሰረት 1 መቶ የሚሆኑ ህፃናት በዚህ ችግር ምክንያት ክትባቱን አላገኙም ተብሎ እንደሚታመን ጠቁመዋል፡፡
የልጅነት ልምሻ /ፖሊዮ/ ክትባት በቢሮው በኩል በዘመቻ በየአመቱ የሚሰጥ ቢሆንም ክትባቱን ያላገኙ ህፃናት ካሉ እንዲሁም የፖሊዮ በሽታ ምልክቶችን የሚታይባቸው ህፃናት ካሉ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች በ6406 አጭር የስልክ መስመር በመደወል ጥቆማ መስጠት እንደሚገባቸው የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ዳምጠው ተናግረዋል፡፡
ህጻናት መደበኛ ክትባታቸውን ሳያቋርጡ እንዲወስዱ በማድረግ ወላጆች ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ዳይሬክተሩ በአፅንዖት ተናግረዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ