ታኅሳስ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጅቡቲ በቅርቡ ኢትዮጵያ የታጁራ ወደብን መጠቀም እንደምትችል መግለጿ እና በኢትዮጵያ በኩል ግን ፍላጎት እንዳልተንጸባረቀ ማስታወቋ ይታወሳል፡፡
በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የዲፕሎማሲ እና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ አበራ ሄጲሶ፤ጅቡቲ ኢትዮጵያ የታጁራ ወደብን እንድታስተዳድር መፍቀዷን አስታውሰዋል፡፡
አገሪቱ ይህንን ውሳኔ እንድትወስን ያደረጋት በኢትዮጵያ በኩል የባህር በር ባለቤትነት አሊያም የተጠቃሚነት ጥያቄ በአለም መድረክ ከፍ ብሎ ስለተስተጋባ፤ በቀጠናውም ውጥረት ስለሰፈነ ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ኢትዮጵያ ለጅቡቲ እያቀረበች ያለውን የሃይል አቅርቦት ተከትሎ ሊሆን እንደሚችልም አመላክተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ጥያቄውን በእርጋታ ልታስብበት እንደሚገባ ያብራሩት ባለሙያው፤ በቅድሚያ ግን ከሶማሊያ ጋር እያደረገች ያለውን የወደብ ተጠቃሚነት ጥያቄ መልስ ማግኘት እና የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መደረስ እንዳለበት አመላክተዋል፡፡
የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ ኢትዮጵያ የባህር በር ስታገኝ እቃ ለማጓጓዝ ብቻ ሳይሆን የባህር ሐይሏን ለመገንባት መጠቀም እንደሚገባት ገልጸው፤ በጅቡቲው የታጁራ ወደብ ይህን ማሳካት የምትችልበት እድል ጠባብ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡
የባህር በር ለእርዳታ የሚገቡ እህሎችን ጨምሮ ማዳበሪያ እና ሌሎች ምርቶች ከውጭ በቀላሉ ለማስገባት እንደሚረዳም ተናግረዋል፡፡
ከወራቶች በፊት ጅቡቲ ኢትዮጵያ የታጁራ ወደብን እንድታስተዳድር መፍቀዷ የሚታወስ ሲሆን የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት እጩ ተወዳዳሪው መሀመድ አሊ የሱፍ፤ ሀገራቸው ኢትዮጵያ የታጁራ ወደብን እንድታስተዳድር ባቀረበችው ውሳኔ የአቋም ለውጥ እንዳላደረገች ማረጋገጣቸው የሚታወስ ነው፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ