👉ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ ስለተሰጠዉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ መረጃ እንደሌለዉ ገልጿል፡፡
ታኅሳስ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ትምህርት ሚኒስቴር ከሰሞኑ የፕሮፌሰርነት ማእረግ መስጠት ጉዳይ ላይ እግድ መጣሉ ይታወቃል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ታኅሳስ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ለአምስት ምሁራን የፕሮፌሰርነት ማእረግ መስጠቱን ይፋ አድርጓል፡፡
ዩኒቨርሲቲዉ በህግ እና በአዋጅ በተሰጠው መብት ፤ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ያሉ ምሁራን ህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ተሰብስቦ በወሰነው ውሳኔ መሰረት የተሰጠ የትምህርት ማእረግ እንደሆነና ህጋዊ አካሄድን የተከተለ መሆኑን የዩኒቨርሲቲዉ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ተናግረዋል።
ዩኒቨርስቲዉ ራስ ገዝ በመሆኑ ውስጣዊ አሰራሮቹን በሚመለከት ህጋዊ መንገዶቹን በመጠቀም የሚያደርገው ውሳኔ ላይ ነጻነት እንዳለው የገለጹ ሲሆን የፕሮፌሰርነት ማእረግ የመስጠት ህጋዊ ስልጣን እንዳለዉ አስረድተዋል፡፡
ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በየትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተሰጠ እና የሚሰጥ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ተቀባይነት እንደማይኖረው ትምህርት ሚኒስቴር እገዳ መጣሉ ይታወቃል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰጠዉን የፕሮፌሰርነት ማእረግ ጉዳይ በተመለከተ መረጃ እንደሌላቸዉ የተናገሩት በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ ናቸዉ፡፡
ሚኒስቴር ዴኤታዉ መረጃዉ የለኝም ይበሉ እንጂ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ምላሽ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዳይሰጡ የታገደው ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጣ ጥቆማ መነሻ መሆኑ ገልጸዋል።
በወጣው ደንብና መመሪያ መሰረት የማይሰሩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በመኖራቸው እስካሁን ያለውን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አሰጣጥ እንዲፈተሽ ለማድረግ እና የአካዳሚክ ሠራተኞች የደረጃ ዕድገት መመሪያ በመሻሻል ላይ የሚገኝ በመሆኑ እገዳው መቀመጡን የተናገሩት አቶ ኮራ ፤ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎችን በተመለከተም ተቋማቱ ራሳቸውን የማስተዳደር ነጻነት ያላቸው በመሆኑ ለተቋማቱ ደረጃዎችንና ፖሊሲዎችን ከማዘጋጀት እና የአሰራር ሂደታቸውን ከመፈተሽ ባለፈ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የመስጠት አሰራራቸዉን የማገድ ስልጣን እንደሌለው ገልጸዋል።
ከሰሞኑ የትምህርት ሚኒስቴር ከባለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ የሚደረጉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተቀባይነት የማይኖረውና እንዳይሰጡም እገዳ መጣሉ የሚታወስ ነው። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እግዱ እንደማይመለከተዉ ተገልጿል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ