ታኅሳስ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ነዋይ ገበያ ከመንግስት ግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ በተጨማሪ የኮርፖሬት ቦንድ ሽያጭ ገበያን ወደ ሰነደ መዋዕለ ነዋይ ገበያ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ነዋይ ገበያ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጥላሁን እስማኤል ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮች እና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ጋር የኮርፖሬት ቦንድ ሽያጭ ለመተግበር ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።
ወደ ገበያ ለlመምጣት ፍላጎት ባይኖራቸው እንኳን ያላቸውን ቦንዶች በኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ነዋይ ገበያ ማስመዝገብና ዲጂታል የማድረግ ሃላፊነት እንደሚኖርባቸው እና እንደሚገደዱ ተናግረዋል፡፡
የተቋሙ ዳይሬክተር ዶክተር ጥላሁን ባለፈው አንድ ዓመት ኩባንያውን እውን ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት ሲያከናወኑ እንደነበር ጠቁመዋል።
ኮርፖሬት ቦንድ ወደ ገበያ ሲገባ በቋሚነት የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ሽያጭ፣ ግዥ እና ልውውጥ የሚደረግበት ሲሆን ለመንግሥት እና የግሉ ዘርፍ የገንዘብ ምንጭ በመሆን ለምጣኔ ሀብት እድገት ጠቃሚ መሆኑን ገልፀዋል።
መንግስት እና የግሉ ዘርፍ ለሚያከናውኗቸው ኢንቨስትመንቶች ካፒታል ለማሰባሰብ ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር ይጠበቃልም ነው ያሉት።
በሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ አክስዮን የሚሸጡ ኩባንያዎች በየጊዜው የሂሳብ ሁኔታቸው እየተገመገመ ይፋ የሚሆንበት አሰራር መዘርጋቱ ተጠቁሟል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ