ታኅሳስ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትላንት ታህሳስ 15/2017 ዓ.ም በሀገራዊ ጉዳዮችና በልዩ ልዩ የፓርቲ አጀንዳዎች ላይ የፓርቲው አባላት ውይይት መጀመራቸውን ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮም ከወቅታዊ አገራዊ እና ቀጠናዊ ጉዳይ አንጻር የብልፅግና ፓርቲ አባላት ውይይት ትኩረት ዙሪያ ባለሙያዎችን አነጋግሯል፡፡
ፓርቲው በሚያደርገው ውይይት አገራዊ የሰላም ጉዳይ፤ የኢኮኖሚያዊ ችግር እንዲሁም ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጉዳይ በስፋት ሊዳሰስ ይገባል ያሉት የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ባለሙያው ዶክተር አየነው ብርሀኑ ናቸው፡፡
አባላቱ ፖለቲካዊ አለመግባባቶች በሚፈቱበት ጉዳይ ዙሪያ ሊነጋገሩ እንደሚገባ እና ከታጣቂዎች ጋር የሚደረጉ ጅምር የሰላም ስምምነቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ማድረግ እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡ በዜጎች ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያስከተለ ያለው የኑሮ ውድነትም ውይይት ተደርጎበት ቀጣይ አቅጣጫ ሊቀመጥ ይገባልም ብለዋል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት የሰጡት ሌላኛው የፖለቲካ ባለሙያ አቶ ጌትነት ወርቁ ብልፅግና ፓርቲ በሚያደርገው ውይይት ሀገራዊ ሰላም እና የደህንት ጉዳይን በትኩረት መመልከት እንደሚገባው አመላክተዋል፡፡
እንደ ሀገር በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች እልባት እዲያገኙ ከታጠቁ ሀይሎች ጋር ሰላማዊ ስምምነት ላይ ማተኮር እንደሚያስፈልግም አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
ሀገር እንድትቀጥል በተለያዩ መልኩ የሚታዩ ችግሮች ከውይይት ባለፈ እልባት እንዲያገኙ መስራት እንደሚገባ ነው ባለሙያዎቹ የጠቆሙት፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ