ታኅሳስ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኦሮሚያና አማራ ክልል ባሉ ህዝቦች መካከል ዳግም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማስጀመር ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አባ ገዳና ሃዳ ስንቄ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ተጀምሮ የነበረውና አሁን ላይ በክልሎቹ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት መቀዛቀዞች የሚስተዋልበት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ዳግም ለማስጀመርና ክልሉ ወደ ሠላማዊ ሁኔታ እንዲመለስ ለማድረግ በኦሮሚያ አባ ገዳዎችና ሃዳ ስንቄዎች በኩል እንቅስቃሴ መጀመሩን አባ ገዳ ቃሲም ሁሴን ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ በትግራይ ክልል ጋርም የህዝብ ለህዝብ መቀራረቦችን ለመፍጠር ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
አሁን ላይ በኦሮሚያ ክልል በታጣቂዎች ጋር የተደረሰው ስምምነት በሌሎች የሀገሪቷ አከባቢዎችም ተግባራዊ እንዲደረግ ውይይቶች መኖራቸውን አመላክተዋል፡፡
መንገዶች ምቹ የሚሆኑ ከሆነ ወደ ክልሉ በማቅናት ከክልሉ ህዝብ ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ሃዳ ስንቄ ሳራ ዱቤ በበኩላቸው በመላው ሀገሪቷ ሠላም እንዲመጣ ሁሉም ተባባሪና ፊቃደኛ መሆን እንደሚገባው አስረድተዋል።
የአንድ እናትና አባት ልጆች ጎራ ለየተው መዋጋትን መተው እንዳለባቸውና የሀገር ሽማግሌዎችን ጥሪ ተቀብለውና አክበረው ወደ ንግግር መቅረብ እንዳለባቸው ተማፅነዋል፡፡
በመላው ሀገሪቷ ሠላም እንዲሰፍን ለማድረግ የሀይማኖት ተቋማት ፤ የሀገር ሽማግሌዎች ኃላፊነጻቻን እንዲወጡ መንግስትም ሚናቸውን እንዲወጡ መንገዶችን ማመቻቸት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ