ታኅሳስ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል በጦርነት ምክንያት ተማሪዎች በመደበኛ የትምህርት ሰዓት እየተማሩ አለመሆኑ እና የፈተና ሰዓትም ጠብቀዉ እየተፈተኑ አለመሆኑ ይታወቃል፡፡
በጦርነቱ ምክንያት ለተስተጓጎለዉ የትምህርት ስረዓት ለተማሪዎች የማካካሻ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ያልተሸፈነውን የትምህርት ምዕራፍ በመከለስ እንዲሁም በትምህርት ገበታ ላይ ያልተካተቱትን በማካተት ሲማሩ ቆይተው ለፈተና ዝግጁ መሆናቸው ተረጋግጦ ከጦርነቱ በኃላ ለአራተኛ ጊዜ የተሰጠዉ የሰምንተኛ ክልል አቀፍ ፈተና ታህሳስ 11 2017 ዓ.ም እንደተጠናቀቀና ሁለተኛው ዙር ሰኔ መጨረሻ 2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አ/ቶ እስማኤል አብዱራህማን ለመናኸሪያ ሬዲዲ ገልፀዋል።
የማካካሻ ትምህርቱን ወስደዉ ለስምንተኛ ክልላዊ ፈተና ይቀመጣሉ ተብሎ ከሚጠበቀዉ ቁጥር 50 በመቶ ያህሉ አለልተገኙም ያሉት የትምህርት ቢሮ ምክትል ሃለፊ አቶ እስማኤል ዋነኛዉ ምክንያት ተማሪዎቹ ስደት በመዉጣታቸዉ አንደሆነ አስረድተዋል፡፡
በ2017 ዓ.ም በክልሉ የሚደረገዉ የመጨረሻ የማካካሻ መርሃ -ግብር እንደሆነ ገልጸዉ በቀጣይ አመት ወደ መደበኛው የትምህርት ስርአት እንደሚመለሱም ተናግረዋል፡፡
የትምህርት ባለሙያ ፕሮፌሰር ያለው እንዳወቅ በሀገሪትዋ በትምህርት ስርዓት ዉስጥ ፈተና የሚሰጠው ሙያዉን በተከተለ መንገድ ሳይሆን የተለያዩ ግዓቶች በተጓደሉበት እና የትምህርት መርሃ ግብሩን በሚገባ ሳይከታታሉ እንደሆነ አንስተዋል፡፡
በተለይ ጦርነት በነበረባቸዉ እና ባለባቸዉ አከባቢዎች ይህ በመሆኑ ምክንያት አሁንም በማካካሻ ፈተና መሰጠቱ ተገቢ ቢሆንም የወሰዱት ማካካሻ በተገቢዉ መንገድ የተተገበረ ባለመሆኑ የሚጠበቀዉ ዉጤት ዝቅተኛ ሊሆን እንደሚችል አመላክተዋል፡፡
በትግራይ ክልል በነበረዉ ጦርነት ምክንያት ባለፉት ሶስት አመታት የትምህርት መርሃ ግብሩ በመደበኛ ስርዓት እየቀጠለ አለመሆኑ ይታወቃል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ