ታኅሳስ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ማዕከል ናሳ የገነባት መንኮራኩር የጸሐይን ውጫዊ ከባቢ አየር መቅረብ እንድትችል ከፍተኛ ሙቀትና ጨረር የመቋቋም አቅም እንዲኖራት ተደርጋ መገንባቷን ማዕከሉ አስታውቋል፡፡
ከየትኛውም አይነት የግንኙነት መንገድ ለቀናት ርቃ ያለችው መንኮራኩሯ ሙቀቱን ተቋቁማ ጉዞዋን ቀጥላ ከሆነ ከነገ በስቲያ መልዕክት እንደምትልክ ሳይንቲስቶቹ አስታውቀዋል፡፡
በአሁኑ ሙከራቸውም የፀሐይ ተፈጥሯዊ ሁኔታ እንደሚመስል ይበልጥ ለመረዳት የሚያስችል ግኝት ይኖራል የሚል ተስፋ ሰንቀዋል፡፡ የናሳ ሳይንቲስቶች ኃላፊ ዶክተር ኒኮላ ፎክስ “የሰው ልጅ ለበርካታ ምዕተ ዓመታት የፀሐይን ሁኔታ ለማጥናት ሙከራ ሲያደርግ ነበር፣ ይሁንና የአንድን ቦታ ትክክለኛ ሁኔታ ለመረዳት በአካል ሔዶ መመልከትን የመሰለ የለም” በማለት ነበር ስለ ጥናቱ አላማ የገለጹት፡፡
“ፓርከር ሶላር ፕሮብ” በሚል ስያሜ በ2018 ይፋ የተደረገው የፀይን ተፈጥሮ ይበልጥ የመመርመር ዓላማ ይዞ ከተቋቋመ ወዲህ 21 ጊዜ ወደ ጸሐይ ለመቅረብ ያለሙ የጠፈር ጉዞዎች ያደረገ ሲሆን በፈረንጆቹ ገና ዋዜማ የተደረገው የአሁኑ ሙከራ ከምድር እጅግ የቀረበው ሲሆን 150 ሚሊየን ኪሎ ሜትር ያሕል ርቃ ወደ ምትገኘው ፀሐይ እስከ 6 ነጥብ 2 ሚሊየን ኪሎ ሜትር መቅረብ አስችሏል ያው የቢቢሲ ዘገባ ነው፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ