ታኅሳስ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከ2016 ዓ.ም የክረምት ወራት መግባት ጋር ተያይዞ አጠቃላይ የጥገና ሥራ ሲያከናውኑ የቆዩት ስኳር ፋብሪካዎች መደበኛ የማምረት ሥራቸውን መጀመራቸው ተገለጸ፡፡
የፋብሪካዎቻቸውን የተለያዩ ማሽነሪዎችን፣ የእርሻና የመስኖ ማሽነሪዎች እንዲሁም የመስኖ አውታር አጠቃላይ የጥገና ሥራዎችን በክረምቱ ወራት አከናውነው ስኳር ማምረት የጀመሩት ስኳር ፋብሪካዎች ወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ፣ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3/1 እና ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካዎች ሲሆኑ የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካም የክረምት ወራት አጠቃላይ የጥገና ሥራውን አጠናቆ ወደ ኦፕሬሽን እየገባ ነው ተብሏል፡፡
ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የክረምት ጥገና ሥራውን አጠናቆ ምርት ማምረት ከጀመረ አንድ ወር ያለፈው ሲሆን ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ከሶስት ሳምንት፣ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 እና መተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከሁለት ሳምንት በፊት የክረምት ጥገና ሥራቸውን አጠናቀው ወደ ምርት ገብተዋል፡፡በተመሳሳይ ሁኔታ የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ ሰሞኑን የክረምት ጥገና ስራውን አገባዶ ወደማምረት ስራ እየገባ እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡
በእስከአሁኑ ሂደት ፋብሪካዎቹ ከ300ሺ ኩንታል የሚበልጥ ምርት ማምረት ችለዋል፡፡ በዚህም ወንጂ ስኳር ፋብሪካ በቀን እስከ 7ሺ ኩንታል ስኳር ማምረት ወደቻለበት ውጤታማ የአፈጻጸም ደረጃ መድረስ የቻለ ሲሆን ሌሎቹም በተመሳሳይ ሁኔታ በቀን አሁን ከደረሱበት ማለትም በቀን በአማካይ 3ሺ ኩንታል ከፍ እያሉ እንደሚሔዱ ይጠበቃል፡፡ የጉልበት ሰራተኞች አቅርቦት ችግር በአሁኑ ወቅት ፋብሪካዎቹን እያጋጠማቸው ያለ ጎላ ያለ ችግር መሆኑን ማየት የተቻለ ሲሆን የሰው ሐይል ከሚገኝባቸው ክልልች ጋር ተቀርርቦ በመስራት ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አመቻቺነት መንግስት በበጀት ዓመቱ ለስኳር ፋብሪካዎች የውጭ አገር መለዋወጫ ግዢ የሚውል 27 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር መድቦ ከዚህ ውስጥ እስካሁን 10 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚደርስ የመለዋወጫ ግዢ ተከናውኗል ሲል የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አስታውቋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ