ታኅሳስ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በከተማዋ የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግዙፍ ህንጻ የሚያከራዩ እና ሪል-ስቴት ባለቤቶች የአከራይ ተከራይ ግብር እንዲከፍሉ ስራዎች መጀመራቸዉን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልጿል፡፡
በአዲስ አበባ የሚገኙ ህንጻዎች ሪልስቴት ፥ ለኤምባሲ እና ለተለያዩ ድርጅቶች የሚከራዩ ቪላ ቤቶች እና ተመሳሳይ የሆኑ ለኪራይ የሚዉሉ ቤቶች እና ህንጻዎች የሚጠበቅባቸዉን የአከራይ ተከራይ ግብር እየከፈሉ አለመሆናቸዉን የከተማዋ ገቢዎች ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታወቋል።
በከተማዋ የሚገኙ አብዛኛዎቹ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፥ የትላልቅ ህንጻዎች እና የሪልእስቴት ባለቤቶች ትክክለኛውን የአከራይ ተከራይ ግብር እየከፈሉ አለመሆናቸውን የቢሮው ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ተናግረዋል።
በጋራ መኖሪያ ቤቶች የአከራይና ተከራይ ውል ቢኖርም ትክክለኛውን ግብር የማይከፍሉ አካላት አሉ ያሉት አቶ ሰዉነት ተገቢዉ አከራይ ተከራይ ግብር እንዲከፈል ለማድረግ ጥናቶች ተጠናቀዉ ተግባራዊ የማድረጉ ስራ መጀመሩን አስረድተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በማንኛዉም ዘርፍ ግብር በማይከፍሉ ፤ በሚሰዉሩ ተቋማት እና ግለሰቦች ላይ የሚወስደዉን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
በከተማዋ የቤቶች ኪራይ ላይም ሆነ በሌሎች የንግድ ዘርፎች ላይ የሚደረጉ የታክስ ስወራዎችን ቢሮው ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ