ታኅሳስ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝዉዉር በየጊዜዉ እየጨመሩ ካሉ ህገ-ወጥ ድርጊቶች መካከል እንደሆነ ይገለጻል፡፡
የፌዴራል ፓሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ጄይላን አብዲ፤ ይህን በኬላዎች እና በተለያዩ የሃገሪቱ አከባቢዎች እየጨመረ የመጣዉን ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝዉዉር ለመግታት በአሁኑ ሰዓት ኮሚሽኑ የጦር መሳሪያዎችን በተገቢዉ መንገድ ማስተዳደር የሚቻልባቸውን አሰራሮች በመቅረጽ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በዚህም በህገ-ወጥ መልኩ የሚያዙ መሳሪያዎች በምን መልኩ መቀመጥ እና መያዝ እንደሚኖርባቸው በማድረግ ውስጥ ሚና እንደሚኖረው አንስተው፤በተቻለው መጠን የሚያዙ የጦር መሳሪዎችን መነሻ በማድረግ ኮሚሽኑ ምልክቶች እንዲቀመጡባቸው እና ያላግባብ ከተቋሙ እውቅና ውጪ መንቀሳቀስ እንዳይችሉ የሚደረግባቸዉ የዉስጥ አሰራሮች እየተዘረጉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
አያይዘውም ተቋሙ በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ ያሉ የጦር መሳሪያዎችን ማስተዳደር እንዲቻል የምዝገባ ስራዎች ሊያካሂድ ስለመሆኑ አስታውቀው፤ በተለይም በኬላዎች ላይ እየታየ ያለውን የህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎች ዝዉዉርን እና ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ ወንጀሎችን መነሻ በማድረግ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ይሁን እንጂ አሁንም ድረስ በተለያዩ መንገዶችና ሀገራት በኩል ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎች እየገቡ መሆኑን ገልጸዉ በቀዳሚነት ከደቡብ ሱዳን ፤ከጅቡቲ እና ከጎረቤት ሀገራት በኩል ይህ አይነቱ ችግር በስፋት እየታየ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን መግታት እንዲቻል በማህበረሰቡ በኩል የሚሰጡ ጥቆማዎች አስፈላጊ መሆናቸው የተገለጹት አቶ ጄላን ያለዉን ችግር ለመግታት አዳዲስ የቁጥጥር ስራዎች ተግባራዊ እንደሚደረጉ አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ