ታኅሳስ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዜጎችን ሰላም ለማስፈን በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ምክክር አስፈላጊ መሆኑን በኦሮሚያ ክልል የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ እየተሳተፉ የሚገኙ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እያለ የሚጠራው ቡድን አባላት ገልጸዋል፡፡
በቅርቡ ከመንግስት ጋር የሰላም ስምምነት የተፈራረመው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እያለ የሚጠራው ቡድን ከፍተኛ አመራር ጃል ሰኚ ነጋሳ የምክክሩን አስፈላጊነት አፅንኦት ሰጥቶ፣ የኦሮሞ ህዝብም ምክክሩ ሰላም ያመጣል የሚል እምነት እንዳለው ገልጿል፡፡
ምክክሩ ምሉዕ የሚሆነው ሁሉም ዜጋ ሲሳተፍበት መሆኑን የተናገረው አመራሩ፤ ለዚህም ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ሁሉ እንደነሱ የሰላም ስምምነት ፈፅመው በዚህ የምክክር መድረክ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ