ታኅሳስ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አሊ ኦማር የተመራ የሶማሊያ ሪፐብሊክ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ እንደሚገባ ተገልጿል።
የልዑኩ የአዲስ አበባ ጉብኝት በዋናነት በቅርቡ በኢትዮጵያና በሶማሊያ መንግስት መካከል የተደረሰውን የአንካራ ስምምነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ልዑኩ በመዲናዋ በሚኖረው ቆይታ የኢትዮጵያና የሶማሊያ ግንኙነትን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚያደርግ ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም ልዑኩ ከኢትዮጵያ አቻው ጋር በሁለቱ ሀገራት ትብብር፣ የእርስ በርስ መከባበር እንዲሁም በቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ የጋራ ፍላጎቶች ላይ ውይይት እንደሚያደርግ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ