👉ሰሜናዊ ጋዛን ለማጽዳት ያለመው እንቅስቃሴ
በመካከለኛው ምስራቅ ይካሔድ እንጂ የሚፈጥረው ምጣኔ ሃብታዊና ማሕበራዊ ቀውስ መላውን ዓለም ያዳረሰው የእስራኤል ሀማስ ግጭት አራት ሀገራትን በተኩስ ልውውጡ ውስጥ ያካተተ ሲሆን የሀማስና የሊባኖሱ ሒዝቦላህ ዋና የድጋፍ ምንጭ የሆነችው ኢራን ለጊዜው ጸጥታን የመረጠች ይመስላል፡፡
በሰሜናዊ እስራኤል ጥቃት እየሰነዘረ ቴላቪቭን እረፍት ነስቷት የነበረው ሒዝቦላህ የደረሰበት ጥቃት ለሊባኖሳውያን ጭምር መትረፉ የቡድኑ እንቅስቃሴ በተኩስ አቁም እንዲገታ አድርጎታል፡፡
እነዚህ ምቹ ሁኔታዎች በሙሉ ኃይሏ ሀማስን እንድታጠቃ እድል የፈጠረላት እስራኤል ታዲያ ሰሜናዊ ጋዛን ለማጽዳት ያለመ እንቅስቃሴ ጀምራለች ሲሉ ፍልስጤማውያኑ ይከሳሉ፡፡ ነገሩን የምታስተባብለው ቴላቪቭ ግን ጥቃቷን ቀጥላለች፡፡
የዛሬው ዓለም አቀፍ ትንታኔያችን ጉዳዩን በሰፊው ቃኝቶታል።
ምላሽ ይስጡ