ታኅሳስ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ፤ ባሳለፍነው ሳምንት ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮች ጋር ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት አባልነት ራሷን ዕጩ አድርጋ ማቅረቧን መግለፃቸው የሚታወስ ነው፡፡
የአለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ እያሱ ሃይለሚካኤል ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት አባልነት እጩ ሆና መቅረቧ ለዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ብሎም አህጉራዊ የጸጥታ ችግሮችን ከመፍታት አንፃር ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደመሆኗ የሚፈጠሩ ግጭቶችን በመፍታት ረገድ ተመራጭ ያደርጋታል ያሉት መምህሩ በሌላ በኩል የአፍሪካን ችግር በአፍሪካውያን የሚለውን መርህ ለማስቀጠል ብሎም የሌሎች አለም ሃገራትን ጣልቃ ገብነትን በማስቀረት ለአህጉሩ ችግር መፍትሄ ለማበጀት በሚሰራው ስራ አዎንታዊ ሚና ይኖራታል ብለዋል፡፡
የስነ አመራርና የፖለቲካ መምህሩ አቶ ጌትዬ ትርፌ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ከታሪኳ እና አህጉራዊ የሰላም ማስከበር ስራ ላይ ካላት አበርክቶ አንጻር ምክንያታዊ ጥያቄ ነው ብለዋል፡፡
ሃገራችን የጸጥታው ምክር ቤት አባል ብትሆን በሃገር ውስጥ ያለባትን የሰላም ማስከበር ስራ በማጠናከር የጎረቤት ሃገራትን የሰላምና ፀጥታ ችግር ለማስጠበቅ ትልቅ ሃላፊነት የሚኖራት በመሆኑ የተጠናና የተጠናከረ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አባል መሆኗ አህጉራዊም አገራዊም ጠቀሜታ እንደሚኖረው ነው ባለሙያዎች የገለጹት።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ