ታኅሳስ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የምርጫ ቅስቀሳ በሚያካሂዱበት ወቅት በቲክቶክ በቢሊዮን የሚቆጠር እይታ ማግኘታቸውን የገለጹት ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሳይዘጋ ለተወሰነ ጊዜ እንዲቆይ እንደሚፈልጉ በትናንትናው እለት ተናግረዋል።
ትራምፕ ወግ አጥባቂ ደጋፊዎቻቸው በተገኙበት በአሪዞና ፎኒክ የሰጡት አስተያየት ቲክቶክ ከአሜሪካ ገበያ እንዲወጣ እንደማይፈልጉ የሚያሳይ ነው ተብሏል።
የአሜሪካ ሴኔት ባለፈው ሚያዝያ ወር ቲክቶክ የብሔራዊ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በመጥቀስ ነበር ንብረትነቱ የቻይናው ባይቲዳንስ የሆነውን መተግበሪያ በአሜሪካ ውስጥ እንዲሸጥ ወይም አንዲታገድ የወሰነው።
የቲክቶክ ባለቤቶች ጉዳዩ በህግ እንዲታይላቸው የሚፈልጉ ሲሆን የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ጉዳዩን ለመስማት ፍቃደኛ ሆኗል። ነገርግን ፍርድ ቤቱ ባይቲዳንስ የሚፈልገውን ውሳኔ ከላሳለፈ እና የድርሻ ሽያጭ የማይከናወን ከሆነ መተግበሪያው ትራምፕ በዓለ ሲመት ከመፈጸማቸው በፊት አሜሪካ ውስጥ ሊታገድ ይችላል።
ትራምፕ ሴኔቱ በአብላጫ ድምጽ ቲክቶክ እንዲሸጥ ያሳላፈውን ውሳኔ እንዴት እንደሚቀለብሱት ግልጽ አይደለም።
“ማሰብ ያለብን ይመስለኛል፤ ምክንያቱም እንደምታውቀት ቲክቶክ በምንጠቀምበት ወቅት በቢሊዮኖች በመታየት በጣም ጥሩ የሚባል ምላሽ አግኝተንበታል” ሲሉ ትራምፕ “አሜሪካ ፈርስት” ለሚሉት ወግአጥባቂ ደጋፊዎቻቸው መናገራቸውን አል አይን ዘግቧል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ