ታኅሳስ 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በስያትል አካዳሚ ፤ በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ እና በስራና ክህሎት ሚኒስቴር አጋርነት የሚዘጋጀው ኤ አይ ፎር ጉድ ኢትዮጵያ የወጣቶችና የታዳጊዎች ውድድር በመጭው መጋቢት ወር በሳይንስ ሙዝየም ላይ በሚዘጋጀው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር 5 ሺህ ታዳጊና ወጣቶችን ያለምን ክፍያ እንደሚያሳትፍ የኤ አይ ፎር ጉድስ ፕሮጀክት ሃላፊ ሄለን አቢ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዉ መግለጫ አስታዉቀዋል፡፡
በመጭው መጋቢት የሚዘጋጀው ውድድር የአሸናፊዎች አሸናፊ የሆኑትን በመምረጥ ወደ ጀኔቫ በማቅናት 40 ሀገራት ከሚሳተፉበት የዓለም አቀፉ መድረክ ተሳታፊ ለማድረግ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ጀኔቫ ላይ ከሚወዳደሩ 40 ሀገራት ውስጥ ናሽናል ኤቨንት እንዲያዘጋጁ ከተመረጡት 25 ሃገራት አንዷ ኢትዮጵያ ነች ያሉት ደግሞ የስያትል አካዳሚ ስራ አስኪያጅ እና የኤ አይ ፎር ጉድስ የኢትዮጵያ ተወካይ መንግስቱ ወዳጀ ናቸው፡፡
አክለውም ተቋሙ ከአሁን በፊት በ500 ወጣቶችና ታዳጊዎች ከ100 በላይ ፕሮጀክቶችን አዘጋጅቶ 25 ፕሮጀክቶች ተቀባይነት አግኝተው ለኤግዚቪሽን እንደቀረቡም አስታዉሰዋል፡፡
በመግለጫው የስያትል አካዳሚ ስራ አስኪያጅ እና የኤ አይ ፎር ጉድስ የኢትዮጵያ ተወካይ ፤ የኤ አይ ፕሮጀክት ሃላፊ ፤የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኤር እስፔስ ኢንጅነር እና የኡጋንዳ ተወካይ የሆኑት ሰለሞን ቦይሬ ተገኝተዋል፡፡
ውድድሩ 84 ቀናት ብቻ የቀሩት ሲሆን ዝንባሌ ያላቸውን በውድድሩ በመሳተፍ የሀገርን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ለማስተዋወቅ እንዲሁም የሀገራችን ኢትዮጵያ ወጣቶች ያላቸውን አቅም ለማሳየት ትልቅ እድልን እንደሚፈጥር ተመላክቷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ