ታኅሳስ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቀበና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኙ ከ500 በላይ የሚሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች ከትምህርት ቤቱ እንዲወጡ መደረጉን ተቋሙ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ ባለው የወንዝ ዳር ፕሮጀክት የቀበና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ሊፈርስ መሆኑንና በትምህርት ቤቱ የሚገኙ 570 የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች በኮከበ ፅባህ ሁለተኛ ደረጃና መሠናዶ ትምህር ቤት መቀላቀላቸውን የቀበና መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ሻምበል ኦልጅራ ተናግረዋል፡፡
ተማሪዎቹ ከታህሳስ 9/2017 ዓ.ም ጀምሮ በኮኮበ ፅብዓ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ቀድሞ በነበሩ የመማር ማስተማሪያ ክፍሎች ውስጥ ትምህርታቸውን እንደጀመሩ ገልፀዋል፡፡
ተማሪዎቹ ቀድሞ በነበረው ትምህርት ቤታቸው የሚያገኙት የምገባ አገልግሎት ሳይቋረጥ መቀጠሉንም ርዕሰ መምህሩ አስታውቀዋል፡፡
እስካሁን ለትምህርት ቤቱ ተለዋጭ ቦታ እንዳልተሰጠ የተናገሩት የቀበና መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ሻምበል ኦልጅራ፤ በኮከበ ፅባህ ሁለተኛ ደረጃና መሠናዶ ትምህርት ቤት እስከመቸ እንደሚቆዩም የተነገራቸው ነገር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ