♻️ከ2መቶ 78ሺህ ብር በላይ ከደንበኞች አካውንት በመቀነስ ለግል ጥቅሙ ያዋለ የባንክ የደንበኞች አገልግሎት ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ውሎ ክስ መመስረቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
ታኅሳስ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ተከሳሹ ግለሰብ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በሻሌ 72 አካባቢ ከሚገኝ የግል ባንክ ውስጥ የደንበኞች አገልግሎት መኮንን ሆኖ በሚሰራበት ባንክ ውስጥ በተደጋጋሚ ከተለያዩ ግለሰቦች የባንክ ሂሳብ ወደ ግል ሂሳቡ በሞባይል ባንኪንግ እና በቀጥታ በማስተላለፍ ሲጠቀም እንደነበረ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የበሻሌ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ገልጿል።
ግለሰቡ በቁጥጥር ስር እስከ ዋለበት ጊዜ ድረስ ከ5 የባንኩ ደንበኞች ያለ ፈቃዳቸው ከግል ሂሳባቸው 2መቶ 78 ሺህ 6 መቶ 91 ብር ከ7 ሳንቲም (278.691.7 ) በጥሬ ገንዘብ ወጪ በማድረግ፣ ከሂሳብ ወደ ሂሳብ እና በሞባይል ባንኪንግ በማስተላለፍ የወሰደ መሆኑ በምርመራ መረጋገጡን እና ተከሳሹ ያለ ምንም ተፅዕኖ በሰጠው የእምነት ቃል በተደጋጋሚ ድርጊቱን የፈፀመ መሆኑን ያመነ ሲሆን ድርጊቱ የኃላፊዎቹን አለመኖር በመጠቀም ለደንበኞች መልዕክት እንዳይደርስ ሲስተም ላይ የራሱን ስልክ ቁጥር በማስገባት በፈፀመው ወንጀል ክስ እንደተመሰረተበት ተገልጿል።
ተከሳሹ የአንደኛ የግል ተበዳይ ለወላጅ አባታቸው በባንክ ቤቱ በአካል ቀርበው ገንዘብ አስተላልፈው ሊሄዱ ሲሉ ስልኮትን ይስጡኝ ሞባይል ባንኪንግ እንዲጠቀሙ ላስተካክል በማለት ተቀብሎ ለኃላፊው የግል ተበዳይ የስልክ ቁጥር መቀየራቸውን ዋሽቶ በመግለፅ አዲስ ስልክ ላይ መልዕክት እንዲደርሳቸው ጠይቀውኛል በማለት ኃላፊውን በማታለል የራሱን ስልክ በመሙላት ከ35ሺህ ብር በላይ ወደ ግል ሂሳቡ ያስተላለፈ እና የሌሎችን ግለሰቦችንም ስልክ ቁጥር በመቀየር የተጣለበትን ኃላፊነት ወደ ጎን በማለት በፈፀመው ወንጀል አንደኛ ከሳሽ ወደ ፖሊስ ጣቢያው ቀርበው ባመለከቱት መሰረት በቁጥጥር ስር ሊውልም ችሏል።
በግልም ሆነ በመንግስት ባንኮች ላይ ያሉ ኃላፊዎች በተገቢው የኮምፒተራቸውን ሚስጥራዊ ቁጥር በመሰወር እንዲሁም በሰራተኞቻቸው ላይ ተገቢውን ቁጥጥር የማድረግ ስራ በመስራት ከደንበኞቻቸው የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመቀበል ሊሰሩ እንደሚገባና ህብረተሰቡም የባንክ ሂሳቡን ሲያንቀሳቅስ በስልኩ ላይ ምንም አይነት መልዕክት ካልደረሰው በአካል ወደ ባንኩ ቀርቦ ሊያመለክት እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ