ታኅሳስ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይህ ፈረንሳዊ የቡድኑ አምበል የኮንትራት ሁኔታው አሳሳቢ እንደሆነ ይታወቃል። በ2026 ውሉ ይጠናቀቃል ስለዚህ ውሉን እንዲያድስ ለማድረግ የሄዱበት ርቀት እና የሞከሩት ሙከራ የከሸፈ ይመስላል።
በዚህ የተናደደ የሚመስለው ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ፎንሴንካ በጣልያን ሴሪያ ሮሳነሪዎቹ ከጄኖአ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ተጫዋቹ ከስብስቡ ውጪ እንዳደረገው አይዘነጋም። አሁንም ታዲያ ቡድኑ ነገ ወደ ባንቴጎዲ ተጉዞ ከሄላስ ቬሮና ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ላይ ቲኖን አስቀምጠው እድሉን ለአሌክስ ሄምኔዝ የመስጠት ሀሳብ እንዳላቸው መረጃዎች ጠቁመዋል።
ቲዮ በሳንሲሮ ወጥነት ያለው የሜዳ ሌን እንቅስቃሴ ከሚያሳዩ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው። የሮሳኔሪዎቹ አምበል መሆኑ መዘንጋት የለበትም። በሳንሲሮ የሚያቆየው ውል እስከ 2026 ነው የሚቆየው ውሉን ለማራዘም ወኪሉ ከክለቡ ጋር ንግግሮች ላይ ቢገኝም ተጨባጭ ነገር ግን እስካሁን የለም።
እንደ ጋዜጠኛ ዳኒኤሌ ሎንጎ ዘገባ ከሆነ በሁለቱ ወገኖች በኩል ነገሮች እየከረሩ እንደመጡ እና ቲዮ ለክለቡ ካደረገው ግልጋሎት ይልቅ ክለቡ በራሱ መንገድ መሄድ ሲፈልግ ለተጫዋቹ ባሳዩት ማላሽ ተበሳጭቷል ክለቡንም ለመልቀቅ እያሰበ እኝደሚገኝ ተገልጿል።
ፈረንሳዊው የግራ መስመር ተመላላሽ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ቲዮ ኸርናንዴዝ በ2019 ሪያል ማድሪድን በመልቀቅ ኤሲ ሚላንን መቀላቀሉ አይዘነጋም። ባለፉት 6 የውድድር ዘመናት ይህ ተጫዋች በጣም ወጥነት ባለው መልኩ መልካም ግልጋሎት መስጠቱ አይዘነጋም። የስኩዴቶ ክብሮችንም ማሳካት ችሏል።
የ27 አመቱ ቲዮ በሳምንት 98 ሺ ዩሮ ወይም 82 ሺ ፓውንድ ነው የሚያገኘው ምናልባት በሚቀርብለት አዲስ ውል ሳምንቲዊ ደሞዙ እሱ ባሰበው ደረጃ ካልተሻሻለለት እና ኮንትራቱን ለመፈረም ፈቃደኛ ካልሆነ ያኔ ሮሳኔሪዎቹ በይፋ ቲዮን ለሽያጭ ያቀርቡታል፡፡
ይሄ ፈረንሳዊ አለማችን ላይ በቦታቸው ምርጥ ከሚባሉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው። በማንቸስተር ዩናይትድ እና በሪያል ማድሪድ በጥብቅ እየተፈለገ እንደሚገኝ ይታወቃል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ