ታኅሳስ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለመናኸሪያ ሬዲዮ ቅሬታቸውን ያቀረቡት የእንቅርት መድሃኒት (ታይሮክሲን) ተጠቃሚ መድሃኒቱን የመንግስት መድሃኒት መሸጫ በሆነው ከነማ መደብር በተለያየ ቅርንጫፍ ካሉት መሸጫዎች ተዘዋውረው መጠየቃቸውን እና መድሐኒቱ የለም የሚሉ እንደሚበዙ አስታውቀዋል፡፡
መድሃኒቱ በተገኘበት ፋርማሲም ከወር በፊት 820 ብር ይሸጥ የነበረው ታይሮክሲን አሁን ላይ 3ሺ 200 እየተሸጠ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
በዚህም ምክንያት ታካሚዎች መድሐኒቱን ገዝተው መጠቀም እንዳልቻሉና ሌሎች ጓደኞቻቸው በጤና መድህን ለመግዛት ሲጠይቁ መድሃኒቱ የለም እየተባለ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ መድሃኒቱን ለመግዛት አቅም ስለሌላቸው ለማቆም መገደዳቸውንም ተናግረዋል።
መናኸሪያ ሬዲዮም የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎትን ስለጉዳዩ ጠይቋል፡፡ የአገልግሎቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አወል ሃሰን የመድሃኒት አቅራቢ አገልግሎቱ ለመንግስት ፋርማሲ ብቸኛ አቅራቢ ቢሆንም ሆስፒታሎች ከውጪ የሚያስገቡበት ሁኔታ እንዳለ ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ የመድሃኒት አቅርቦት እጥረት እንደሌለ የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ የተለየ የዋጋ ጭማሪም አለመኖሩን እና ከተቀመጠለት ከ3 እስከ 5 በመቶ ያለፈ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል አስታውቀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር በመሆን የቁጥጥር ስራውን እየሰራ እንዳለም ነው የገለጸው፡፡
ቅሬታ በቀረበበት የታይሮይድ መድሃኒት የዋጋ ጭማሪ ላይ ማጣራትና ክትትል እንደሚደረግበት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የገበያ መረጃ ጥናትና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር አቶ ሙሰማ ጀማል አስታውቀዋል።
መናኸሪያ ሬዲዮ ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ መረጃዎችን ተከታትሎ የሚያቀርብ ይሆናል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ