ታኅሳስ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከሐምሌ ወር ጀምሮ በከተማዋ 15 ሺህ 99 ነጋዴዎች ከንግድ ስርዓቱ መውጣታቸውን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡
47 ሺህ 707 ነጋዴዎች ደግሞ በአዲስ መልኩ የንግድ ፈቃድ አውጥተው የንግድ ስርዓቱን እንደተቀላቀሉ የቢሮው ሃላፊ ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ ተናግረዋል፡፡
ሃላፊዋ በዘንድሮው በጀት ዓመት በ5 ወራት ውስጥ የንግድ ስርዓቱን በአዲስ መልኩ የተቀላቀሉ ነጋዴዎች ቁጥር ከአምና ተመሳሳይ ወቅት በ10 በመቶ እንደጨመረና ከንግድ ስርዓቱ የወጡት ደግሞ በ17 በመቶ መቀነሱን አመላክተዋል፡፡
ቢሮው አዲስ ተመዝጋቢዎችንም ሆነ ከንግድ ስርዓቱ የሚወጡትን በቢሮው በኩል በበየነ-መረብ አማካኝት ክትትል እንደሚያደርግ ነው ኃላፊዋ ያመላከቱት፡፡
በዚህም በአንድ ቀን ውስጥ ምን ያህል ሰው በአዲስ መልኩ እንደተመዘገበና ምን ያህሉ ከንግድ ስርዓቱ እንደወጣ መከታተል ስለሚያስችል በቀላሉ ማወቅ እንደሚቻልም ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ በከተማዋ ያለውን የንግድ ስርዓት ለማስፋፋት እንደ ቢሮ የንግድ ስርዓቱን በማዘመን ለስራው ተግዳሮት የሚሆኑትን በመለየት ለንግዱ ማህበረሰብ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ለመስራት ማቀዱንም ሃላፊዋ አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ