ታኅሳስ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቅርቡ ለኬሚካል ርጭት አገልግሎት የሚውሉ 5 የአውሮፕላን ግዢ መፈፀሙን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስታወቀ ሲሆን 10 ሚሊየን ዶላር ወጪ ስለማውጣታቸውም በወቅቱ ይፋ አድርጓል ፡፡
እንደ ሀገር በሚገጥሙ የአንበጣ መንጋ፤የግሪሳ ወፍ፤ተምች እንዲሁም ለሰብል ምርታማነት ማነቆ በሚሆኑ ጉዳዮች ላይ አዉሮፕላኑ አጋዥ ሆኖ እያገለገለ መሆኑን በግብርና ሚኒስቴር የእጽዋት ጥበቃ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ በላይነህ ንጉሴ ገልጸዋል፡፡
በቅርቡ በሀገሪቱ እንደ ግሪሳ ወፍ እና መሰል የበረሃ አንበጣን መመከት እንዲቻል ግዢ የተፈጸመባቸው አውሮፕላኖች ሚናቸውን እየተወጡ እንደሚገኙም ነው ያነሱት፡፡በዚህም በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ የበረሃ አንበጣ እና ግሪሳ ወፍን በሚመለከት የኬሚካል ርጭት እየተደረገ ስለመሆኑንም አስረድተዋል፡፡
በዚህም ባለፉት ጊዜያት የበረሃ አንበጣ በእጅጉ አሳሳቢ እንደነበር አንስተዉ በተያዘው በጀት አመት አሳሳቢነቱ መቀነሱን ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን ችግሩ የሚከሰት ከሆነ የተገዙት አውሮፕላኖች በምስራቅ አፍሪካ ካለው የበረሃ አንበጣ ድርጅት ጋር በጥምረት ጥቅም ላይ እንዲዉሉ ይደረጋል ብለዋል፡፡
አውሮፕላኖቹ የሚሸከሙት የኬሚካል መጠን እንዲሁም በቴክኖሎጂ የተሳሰሩ መሆናቸውን ተከትሎ ከመደበኛ ስራቸው ባሻገር ለሚከሰቱ ተፈጥሮዓዊ እንዲሁም ሰው ሰራሽ አደጋዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ ስለመሆኑም አስረድተዋል፡፡
እንደ ሀገር ከዚህ ቀደም ከሌሎች ሃገራት ለኬሚካል ርጭት የሚውሉ አውሮፕላኖች በኪራይ ስንጠቀም መቆየታችንና ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሬ እያስወጣ እንደነበር አስታዉሰዋል፡፡ የአውሮፕላን ግዢው ከተደረገ በኋላ ለኪራይ የሚጠይቁ ሃገራት ቁጥር መጨመሩን ገልጸዋል፡፡
ስራ አስፈጻሚው ለሌሎች ሀገራት የሚደረጉ ኪራዮችን ተከትሎ ለአውሮፕላኖቹ ጥገና እና እንደ ገቢ ምንጭም እያገለገሉ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ