ታኅሳስ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ምስራቅ አፍሪካዊቷን ሀገር ሶማሊያን የሚያስተዳድረው መንግስት አሸባሪውን አልሸባብ ለመቆጣጠር ያስችለኛል ያለውን ሕግ በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ተግባራዊ እንዲደረግ አዟል፡፡
ሕጉ የትኛውም የሱቅ ባለቤት በመግቢያ በሩ ላይ የደህንነት ካሜራዎችን እንዲሰቅል አዟል፡፡ ይሁንና የሽብር ቡድኑ ካሜራዎቹን የሚሰቅሉ ነጋዴዎች በነፍሳቸው ይፍረዱ የሚል መልዕክት ማስተላለፉ በርካታ ነጋዴዎችን ትልቅ ስጋት ውስጥ ከቷቸዋል፡፡
ጥቂት የማይባሉትም የንግድ ስፍራዎቻቸውን ሽጠው ቤታቸው መቀመጥ መርጠዋል፡፡ የሀገሪቱ ፖሊስ የደሕንነት ካሜራዎች ያልሰቀሉ ነጋዴዎችን በቁጥጥር ስር እያዋለ ሲሆን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ባለሱቆች በሁለት ወገን ጫና እየደረሰብን ነው ብለዋል፡፡
መንግስት ቡድኑን ለመቆጣጠር የራሱን አማራጭ መጠቀም ይገባዋል ያለ አንድ ስሙ ተቀይሮ አስተያየቱን ይፋ ያደረገ ነጋዴ የቀረቡት አማራጮች በጥይት መመታት ወይም እስር ቤት መግባት የሚሉ በመሆናቸው ሱቁን ሽጦ ቤቱ መቀመጡን አስታውቋል፡፡
ይሁንና የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ሞሐመድ አሕመድ ዲሪዬ የመንግስት እርምጃ የሚታይ ለውጥ ማምጣቱን ገልጸዋል፡፡ እንደ እርሳቸው ገለጻ በወር እስከ አራትና አምስት የቦንብ ፍንዳታ የሚከሰትባት ሞቃዲሾ አሁን ከዚህ ስጋት ተላቃለች ሲሉ ተደምጠዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ