ታኅሳስ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ በመንግስት ተቋማት በኩል የሚሰጡ አገልግሎቶች በበቂ ሁኔታ ተደራሽ አለመሆናቸው ለነዋሪው ትልቅ ችግር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
በመዲናዋ የሚነሳው የአገልግሎት ተደራሽ አለመሆን ችግርን ለመቅረፍ ተቋማት በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ዋና ስራ-አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በፍርድ ቤት የሚወሰኑ የፍቺ እና ጉዲፈቻ ውሳኔዎችን የመመዝገብ አገልግሎት በአንድ ማዕከል መስጠት መጀመራቸው ይህንን ችግር ሊቀንስ የሚያስችል እንደሆነ ያነሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ የምዝገባ ስርዓቱን ተደራሽ ማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ የቴክኖሎጂ አማራጮችን በቅርቡ በመዲናዋ እንደሚተገበሩ ተናግረዋል።
ማህበረሰቡ በሌሎች ተቋማት በኩል የተደራጀ አገልግሎት ማግኘት የሚችልበትን አሰራር ለመፍጠር የከተማ አስተዳደሩ በስራ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በፍርድ ቤት የሚወሰኑ የፍቺ እና የጉዲፈቻ ውሳኔዎችን የመመዝገብ አገልግሎት በአንድ ማዕከል ለመስጠት የሚያስችለውን ስራ ከትላንት ታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ አገልግሎቱን በአራዳ እና በቦሌ ምድብ ችሎቶች ማሰጀመሩ ይታወቃል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ