ታኅሳስ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት እህል ውሀው ሊያበቃ ከጫፍ የደረሰው የ27 አመቱ እንግሊዛዊ እኔ በግሌ ክለቡን ለቅቄ አዲስ ጅማሮ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ፤ ማልፈለግበት ቦታ ቆይቼ ነገሮችን ማባባስ አልፈልግም ፤ ሌሎች ጓደኞቼ ከክለቡ በወጡበት አስከፊ መንገድ የመውጣት ፍላጎት የለኝም ብሎ የተናገረበት bombshell interview ወይም ማንም ያልጠበቀው ፤ አንዳንዶች መስመር ያለፈ ያሉት አይነት ቃለ መጠይቅ ከHenry winter ጋር ማከናወኑን ተከትሎ ፤ ተጫዋቹ በቃ የዩናይትድ ስንብቱን በራሱ እጅ አጣድፎታል በሚል ጉዳዩን እንዲነሳ ምክንያት ሆኗል።
ዩናይትድ ዛሬ ከቶተንሀም ጋር የካራባኦ ካፕ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። ታዲያ አስቀድሞ ቡድኑ ካሪንግተን ላይ ካደረገው ልምምድ በጊዜ አቋርጦ ነው ራሽፈርድ መኪናውን አስነስቶ የሄደው ታዲያ ከጨዋታው በፊት አሰልጣኝ ሩበኝ አሞሪም በሰጠው የPre match press conference ላይ በርከት ያሉ ጥያቄዎች ከራሽፈርድ ጋር በተያያዘ ተጠይቆ ነበር እና መጀመሪያ ልምምድ አቋርጦ የሄደው መጠነኛ የሆድ ህመም ተሰምቶት ነው ያለው አሞሪም ፤ “ራሽፈርድ ስላደረገው ቃለ መጠይቅ ተጠይቆ ፤ እኔ አልሰማሁትም ቃለ መጠይቁን ግን እንደዛ ካለ ትክክል አይደለም ፤ ከስብስቡ የተቀነሰበትን ምክንያት እኔ እነግረው ነበር ፤ ሚድያ ጋር መሄድ አይጠበቅበትም ነበር ፤ ለቡድናችን አስፈላጊ ተጫዋች ነው። ቡድኑ ከራሽፈርድ ጋር የተሻለ ነው። ስለዚህ እኔ በክለቡ ቆይቶ ያለውን አቅም አሳይቶ ፤ ለቦታው ታግሎ ፤ ልዩነቶችን እንዲፈጥር እና ራሱን እንዲያሳይ ነው የምፈልገው” ሲል ሀሳብ ሰጥቷል።
ራሽፈርድ ከ7 አመቱ አንስቶ የካሪንግተን አካዳሚን የተቀላቀለ ተጫዋች እንደሆነ ይታወቃል። በ426 ጨዋታ 138 ጎሎችን አስቆጥሯል። ለሀገሩ እንግሊዝ ደግሞ በተሰለፈባቸው 60 ጨዋታዎች 17 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።
የተጫዋቹ ሁኔታ እስካሁን ሰፊ ርዕስ እየተሰጠው በሚዲያዎች እየተዘገበ የሚገኝ ጉዳይ ነው። ዩናይትድ ዛሬ ወደ ሰሜን ለንደን በማቅናት ምሽት 5:00 ሲል ከቶተንሀም ጋር በካራባኦ ካፕ ሩብ ፍፃሜ የሚገናኙ ይሆናል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ