ታኅሳስ 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከሃምሌ 01 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓ.ም የሚደረገውን የንግድ ፈቃድ እድሳት በወቅቱ ለመጨረስ ነጋዴዎችን ያማከለ የስራ ሰዓት ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ንግድ ቢሮው በከተማው ውስጥ የንግድ ፈቃድ አውጥተው የሚሰሩ ነጋዴዎች የንግድ ፈቃዳቸውን ከሃምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲያከናወኑ ቀነ ገደብ ማስቀመጡ ይታወቃል፡፡ በነበሩት 5 ወራት ውስጥ ንግድ ፈቃዳቸዉን ያደሱ ነጋዴዎች ቁጥር 211 ሺህ 720 ሲሆን፤ቀሪዎቹ ፈቃዳቸዉን ያላሳደሱ ነጋዴዎች ቁጥር 184 ሺህ 733 በመሆኑ በተቀሩት ቀናት እደሳታቸዉን እንዲያከናዉኑ ቢሮዉ አሳስቧል፡፡
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ፤ የንግድ ፈቃዳቸውን ያላደሱ ነጋዴዎች በቀሪ ቀናት ውስጥ የንግድ ፈቃዳቸውን ለማደስ ያለው ጊዜ አጭር ስለሆነና ነጋዴው ለቅጣት እንዳይዳረግ በማሰብ ቢሮው የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን ማዘጋጀቱን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዉ መግለጫ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በፊት ይሰራበት የነበረውን የስራ ሰዓት በማሻሻል ከጥዋቱ 1፡30 እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ድረስ ቢሮውን ክፍት በማድረግ ፤ የቢሮው ባለሙያዎችን በበቂ በማሰማራት ነጋዴው የማህበረሰብ ክፍል እነዚህን ጭማሪ የተደረጉ ሰዓቶችን ተጠቅሞ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ወደ ስራ መግባቱን አስታዉቀዋል፡፡
የስራ ሰዓት ማሻሻያው ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ድረስ እንደሆነና የነጋዴው የማህበረሰብ ክፍልም ይህንን በመገንዘብ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የንግድ ፈቃዱን ማደስ እንዳለበት የቢሮው ሃላፊ ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ አሳስበዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ