ታኅሳስ 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በፍርድ ቤት የሚወሰኑ የፍቺ እና ጉዲፈቻ ውሳኔዎችን የመመዝገብ አገልግሎት ከዛሬ ታኅሳስ 09 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ አገልግሎቱ በአራዳ እና ቦሌ ምድብ ችሎቶች አስጀምሯል፡፡
ከፍቺ እና ከጉዲፈቻ ምዝገባ አገልግሎት በተጨማሪ የፋይዳ ምዝገባ በፍርድ ቤቶቹ እንደሚከናወን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ተናግረዋል፡፡
ተቋሙ በአሁኑ ወቅት የልደት እና ሞት ምዝገባ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በከተማው 104 የመንግስት እና የግል ጤና ተቋማት በመስጠት የምዝገባ ሽፋኑን ወደ 65 በመቶ ማሳደጉን ገልፀዋል፡፡
ከሁለት ሳምንት በኋላ የሚወጣው የፍቺ እና የጉዲፈቻ መረጃ የተረጋገጠ እንደሚሆንም ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡
ይህ አገልግሎት ለሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ብቻ ሳይሆን ለፍርድ ቤቶች አሰራርም ትልቅ ጥቅም እንደሚኖረው የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንት አቶ ፎዓድ ኪያር ተናግረዋል፡፡
በፍርድ ቤቱ አገልግሎት ላይ የመረጃ ጥራት እና የአገልግሎት አሰጣጥ እንደሚጨምር አክለዉ ተናግረዋል።
ሁለቱ ተቋማት የኩነት ምዝገባን ቀጣይነት ለማረጋገጥ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የጋራ ስምምነት ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ