ታኅሳስ 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሱፐር ሊግ በ2021 ሚያዝያ ወር ላይ ሀሳቡ ከተጠነሰሰ በኋላ በርካታ ክለቦች ይህንን ሱፐር ሊግ ተቀላቅለው በነበረበት ሰአት ላይ የአውሮፓ እግርኳስ አወዳዳሪው አካል ወይም UEFA ውድድሩ ውስጥ የሚሳለፉ ክለቦች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ መግለፁን ተከትሎ ከዚህ ውድድር ቀስ በቀስ መውጣታቸው የሚታወስ ነው። የUEFA ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሴፌሪን ኮቪድ ወረርሺኝ እና ሱፐር ሊግ በስልጣን ጊዜያቸው ካሰለቻቸው ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ በሚል አዲስ ሊከናወን የታሰበውን ውድድር ማጣጣሉ አይዘነጋም።
ታዲያ የሱፐር ሊግ መስራቾቹ ጉዳዩን ለስፖርት ገላጋይ ፍ/ቤቱ በመውሰድ ተበድለናል ፊፋ እና ዩኤፍኤ ውድድሩን እንዳናከናውን ከልክለውናል በሚል ያቀረቡት ክስ ሲመረምር ቆይቶ በ2023 ታህሳስ ላይ ገላጋይ ፍ/ቤቱ Uefa እና Fifa ስልጣናቸውን አለአግባብ እየተጠቀሙ ነው በሚል የሱፐር ሊግ ሀሳብ ጠንሳሾች ውድድሩን ማከናወን እንደሚችሉ ማስታወቁን ተከትሎ ውድድሩን በድጋሜ ለመተግበሩ እና እንዲከናወን ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸው አይዘነጋም።
የዚህ የሱፐር ሊግ ምስረታ ዋነኛ አቀንቃኞቹ እና እግርኳሱ ለደጋፊዎች እንጂ ተቋም የሚበለጽግበት መሆን የለበትም በሚል አላማ ውድድሩን ለማስጀመር ቋምጠው የሚገኙት ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ ወደ 50 ክለቦችን ማነጋገራቸው እና ከነዛም መካከል 20 የሚሆኑት ውድድሩ ውስጥ በመቀላቀል መልካም ፈቃድ ማሳየታቸው እየተገለፀ ይገኛል። ክለቦቹ እነማን ናቸው የሚለውን ከመግለጽ የተቆጠቡት የሱፐር ሊግ ዋና ፀሀፊ አናስ ላግሀሪ በቀጣይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውድድሩን በተግባር ላይ ለማዋል ጥረት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
ውድድሩን ለማስጀመር በቂ የክለብ ቁጥር አለን ብለው የሚያስቡት የዚህ ውድድር ምስረታ አቀንቃኞቹ በቀጣይ ወደ አተገባበሩ ለመንደርደር በቂ ነገሮች እንዳሏቸው አምነዋል ተብሏል።
ይሄንን ተከትሎ የአውሮፓ እግር ኳስ አወዳዳሪው አካል UEFA የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የውድድር ቅርፁን በመቀየር የሊግ ፎርማት እንዲይዝ በማድረግ በ36 ቡድኖች መካከል የሚከናወን ውድድር ማድረጉ አይዘነጋም።
የሱፐር ሊግ ሀሳብ ጠኝሳሾች እነሱም ሌላ ለየት ያለ የአጨዋወት መንገድ እና የጨዋታ ቅርጽ ያለው ውድድር ለማዘጋጀት በማሰብ ፕሮፖዛል በመቅረጽ ለUEFA እና FIFA እውቅና እንዲሰጣቸው ደብዳቤ ማስገባታቸው ተሰምቷል።
ታዲያ አሁን መጠሪያቸውን ከሱፐር ሊግ ወደ ዩኒፋይ ሊግ የቀየረ ሲሆን 3 የተለያዩ የሊግ የውድድር ቅርፆች ይኖሩታል ተብሏል። 64 ክለቦችን የሚያካትት በሁለት ሊግ የተከፈለ የወንዶች ውድድር እና 32 ቡድኖችን የሚያካትት የሴቶች ውድድር ይኖሩታል።
በወንዶቹ ውድድር 4 የተለያዩ የውስጥ ሊጎች አሉ። ትልቅ የሚባሉት Star እና Gold league ናቸው። እያንዳንዱ ሊግ ውስጥ 8,8 ቡድኖች ይካተታሉ ፤ ቀሪዎቹ Blue እና union የተባሉ ሊጎች ደግሞ እያንዳንዳቸው 32 ቡድኖችን የሚያካትቱ ይሆናል።
የተለያየ ምድብ ውስጥ የሚገኙ ቡድኖች በደርሶ መልስ ጨዋታቸውን አከናውነው ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡት ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለው በዛ መንገድ አሸናፊው እንደሚለይ የተገለፀ ሲሆን ግማሽ ፍፃሜ እና ፍፃሜ ደርሶ መልስ አይኖራቸውም። ከዛ በተጨማሪ ገለልተኛ ሜዳ ላይ የሚደረጉ ይሆናል።
ሱፐር ሊግ ሲመሰረት 12 ቡድኖችን አቅፎ የነበረ ሲሆን በደጋፊዎች ተቃውሞ እና በእንግሊዝ መንግስት ጣልቃ ገብነት ምክንያት የእንግሊዝ ቡድኖች ራሳቸውን ከዚ ውድድር አርቀው እንደነበር አይዘነጋም። ግን አሁን በተለይ የ2023 የታህሳስ ወር የስፖርት ገላጋይ ፍ/ቤቱ ውድድሩ መከናወን ይችላል ፊፋ እና ዩኤፋ ስልጣናችሁን በአግባብ እንጂ ከልክ በላይ አትጠቀሙ የሚል ውሳኔ ካስተላለፈ እና የክለቦችን ፈቃድ እስካገኘ ፤ህጉን የጠበቀ ፤ ሰላማዊ ውድድር ሆኖ መካሄድ እንደሚችል አረንጓዴ መብራት ካበራ በኋላ የፕሪሚየር ሊግ ፤ ሴሪያ ፤ ላሊጋ ፤ ቡንደስሊጋ ክለቦች በዚል አዲስ የውድድር መድረክ ላይ የመሳተፍ ፍላጎታቸውን አሳይቷል ተብሏል።
የቀድሞ ሱፐር ሊግ ያሁኑ Unify league ብሎ አዲስ ስያሜ እና የአጨዋወት መንገድን ይዞ የመጣው የውድድር ምዕራፍ በFIFA እና UEFa ተቀባይነት እና እውቅና እንዲያገኝ በደብዳቤ ጠይቋል። እንዳይከለከሉ መስፈርቱን ሁሉ ያሟሉ የሚመስሉት የዩኒፋይ ሊግ መስራቾች ጥያቄያቸው ተቀባይነት ያገኛል ወይ የሚለው በቀጣይ የእግርኳስ ቤተሰቡ የሚጠብቀው ጉዳይ ነው።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ