ታኅሳስ 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ከአክሱም ጽዮን ቀጥሎ ሁለተኛው ታላቅ ሥፍራ እንደሆነ የሚነገርለት የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ካስቆጠረዉ እረጅም እድሜ አንጻር አስፈላጊ ዉጫዉ እና ዉስጣዉ እድሳት ሲደረግለት እንደቆየ ይታወቃል፡፡
ለአመታት ሲደረግ የነበረዉ የእድሳት ስራ ወደ መጠናቀቁ በመቃረቡ በሚቀጥለው ጥር ወር ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ቤተክርስቲያኒቱ አስታዉቃለች፡፡የካቴድራሉ አስተዳዳሪ ሊቀ ሥልጣናት ቆሞስ አባ ሲራክ አድማሱ በፌደራል ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን መስሪያ ቤት በኩል በተደረገ ርብርብ አማካኝነት ታዋቂ ባለሞያዎች በማማከር በምን አይነት ሁኔታ መታደስ እንዳለበት ለ17 ወራት ያህል ጥናት ሲደረግ ከቆየ በኋላ በተገኘው ግኝት አማካኝነት እድሳቱ ስለመጀመሩም አስታዉሰዋል፡፡
በዚህም ቫርኔሮ ኮንስትራክሽን ከተባለ የስራ ተቋራጭ ጋር በ172 ሚሊዮን 500 ሺህ ብር በሆነ የሥራ ውል ሥምምነት መፈጸሙን አስታውሰው፤ በአሁኑ ሰዓትም ሥራው በተፋጠነ ሁኔታ ተሰርቶ የውስጥ ስራዎች ወደ ፍጻሜ መድረሳቸውንም አመላክተዋል፡፡በመሆኑም ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ታቦተ ሕጉን ወደ መንበረ ክብሩ ለመመለስ በዝግጅት ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል፡፡
አክለውም በሀገር ደረጃ የተከሰተው የሲሚንቶ እጥረት እና የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት መዘግየት እንዲሁም ከውጪ የሚመጡ መሳሪያዎች በወቅቱ ወደ ሀገር ውስጥ ባለመግባታቸው ለፕሮጀክቱ መጓተት ምክንት እንደነበር አስረድተዋል፡፡ አክለዉም ቀሪ የቤተክርስቲያኒቱ ስራዎች ለማጠናቀቅ የገንዘብ እጥረት እንዳለባቸዉ ተናግረዋል፡፡
የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ-ክርስቲያን የእድሳ ስራዉ እየተጠናቀቀ መሆኑን ቤተክርስቲያኒቱ ዛሬ በሰጠችዉ መግለጫ አስታዉቃለች፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ