ታኅሳስ 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ለመጎብኘት የሄዱ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ባረፉበት ሆቴል አጠገብ ባለ መንገድ ዳር ጥቃቱ መፈጸሙን የከተማው የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጅሃድ ሁሴን ለጣቢያችን ገልጸዋል፡፡
አቶ ጅሃድ ሁሴን ለመናኸሪያ ሬዲዮ እንደተናገሩት በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ የሚካሄደውን የኮሪደር ልማት ለመጎብኘት የሄዱ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ላይ የቦምብ ጥቃት ለማድረስ ሙከራ አድርገዋል በሚል የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል፡፡
በጥቃቱም ሁለት ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ነው የገለጹት፡፡
የቦምብ ጥቃቱ የተፈጸመው፣በከተማው በተለምዶ መርካቶ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደ ስታዲዮም በሚወስደው መንገድ ላይ ሲሆን ይህን ተከትሎ ለተከታታይ ቀናት የሚቀጥል ፍተሻ በተለያዩ የከተማው አከባቢዎች እንደሚኖርም አስታውቀዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ