ታኅሳስ 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኮሪደር ልማቱ ምክንያት በተደረገው ቁፋሮ ተቋርጦ የነበረው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አጭር የስልክ መስመር ዳግም ስራ መጀመሩን ቢሮው ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
ተቋርጦ የነበረው 94-17 ነፃ የስልክ ጥሪ መስመር አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የቢሮው የትራንስፖርት ክትትል እና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ደምሰው ሌሊሳ ናቸው የተናገሩት፡፡
ተገልጋዮች በትራንስፖርት አገልግሎት ዙሪያ ያላቸውን ሃሳብ፣ አስተያየት እና ጥቆማ ለተቋሙ ከሚሰጡበት አማራጭ አንዱ የሆነው ነፃ የስልክ ጥሪ መስመር 9417 መቋረጡ በተገልጋዮች ዘንድ ቅሬታን ያጫረ እንደነበር ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡
ለተወሰኑ ጊዜያት በብልሽት ምክንያት ተቋርጦ የቆየ መስመሩ ዛሬ አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ ተገልጋዮች ሃሳብ፤ አስተያየት እና ጥቆማዎችን በነፃ የስልክ መስመር ጥሪው እንዲያደርሱ ጠይቀዋል፡፡
ከዚህም በኋላ ይቋረጣል የሚል ስጋት እንደሌለ የተናገሩት ዳይሬክተሩ፤ ተገልጋዮችን ለማስተናገድ በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ