ታኅሳስ 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትላንትናው እለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 11ኛ መደበኛ ስብሰባው በኢትዮጵያ ክሪፕቶ ከረንሲን እንደ መገበያያ መጠቀም የተከለከለ መሆኑን የብሄራዊ ባንክ አስታውቋል፡፡
ተሻሽሎ በጸደቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት በተደረገበት እለት ከምክር ቤት አባላት በኩል የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡
በአዋጁ ክፍል 7 አንቀፅ 37 ንዑስ አንቀጽ 1 ስር ክሪፕቶ ከረንሲን ጨምሮ ሌሎች ዲጂታል ግብይቶችን ብሄራዊ ባንክ ካልፈቀደ በስተቀር ማከናወን አይቻልም ይላል አፈፃፀሙ እንዴት ይሆናል የሚለው በምክር ቤቱ አባል በኩል ተነስቷል፡፡
በተለይም አሁን ላይ ዓለም ላይ ዲጂታል መገበያያዎች በስፋት ስራ ላይ እየዋሉ እንደመሆናቸው እንዴት ባለ መልኩ መቆጣጠር ይቻላል የሚለውን አባላቱ ጠይቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ አሁን ላይ በኢትዮጵያ ክሪፕቶ ከረንሲን እንደ መገበያያ መጠቀም የተፈቀደ አይደለም ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ጉዳዩን ለሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ያብራሩት የብሄራዊ ባንክ ገዥው፤ ክሪፕቶ ማይኒንግ አሁን ላይ በኢትዮጵያ በስፋት ስራ ላይ እየዋለ የሚገኝ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ በመሆን እያገለገለ ያለ የኃይል አቅርቦት ስለመሆኑ አብራርተዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ክሪፕቶ ከረንሲን እንደ መገበያያ መጠቀም አይቻልም፤ የዓለም የንግድ ስርዓት ተለዋዋጭ እንደመሆኑ ብሄራዊ ባንክ በሒደት መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላልም ብለዋል፡፡
አሁን ላይ ክሪፕቶ ከረንሲ በበርካታ አገራት በዲጂታል ግብይት ዘርፍ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ እንዳለ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ብሄራዊ ባንክም እንደ ሁኔታው ወደ ፊት እየታየ መመሪያ እስከሚያወጣ ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ መገበያያ መጠቀም የተከለከለ መሆኑን አመላክቷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ