ታኅሳስ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኦሮሚያ ክልል ሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ በአዳማ ከተማ መካሄዱን ቀጥሏል፡፡
ከክልሉ 356 ወረዳዎች የተመረጡ ከ7 ሺህ 500 በላይ የህብረተሰብ ወኪሎች በ4 የተለያዩ ቡድኖች ተከፍለው እንደሚመክሩም ነው የተገለጸው፡፡
በአጀንዳ ማሰባሰቡ መድረክ እየተሳተፉ ያሉ የክልሉ ነዋሪዎች በክልል ብሎም በአገር አቀፍ ደረጃ መሰረታዊ የሚባሉ ጉዳዮችን በአጀንዳነት እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል፡፡ በዚህም አገራዊ ጠቀሜታ ያለው አበርክቶ እንደሚወጡ ነው የገለጹት፡፡
የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሐሙድ ድሪር በበኩላቸው ኮሚሽኑ ሁሉም የሚመለከታቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሒደቱ እንዲሳተፉ ጥሪውን ማቅረቡን ይቀጥላል ብለዋል፡፡
አገራዊ ምክክር በአንድ ጀንበር የሚጠናቀቅ ስራ ባለመሆኑ ኮሚሽኑ ሒደቶችን በመከተል
ም ራሳቸውን ያገለሉ ቡድኖች እንዲሳተፉ ጥሪ ማቅረቡን እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
በክልሉ ከዚህ ቀደም ነፍጥ አንግበው ግጭት ውስጥ የነበሩ እና አሁን ላይ ሰላማዊ አማራጭን የተከተሉ ቡድኖች የወሰኑትን ውሳኔ ኮሚሽኑ በአዎንታዊ መልኩ እንደሚመለከተው የተናገሩት አምባሳደር መሐሙድ ከሌሎቹም የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ቡድኖች ተመሳሳይ እርምጃ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
በተለይ ፓርቲዎች ልዩነት እና የፖለቲካ አቋማቸው እንዳለ ሆኖ በሒደቱ እንዲሳተፉ፤ አጀንዳቸውንም እንዲያቀርቡ ጠይቀዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ እስከ ታህሳስ 15/2017 ዓ/ም እንደሚቀጥል ነው የተገለጸው፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ