ታኅሳስ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በ195ኛው የማንቹሪያን ደርቢ ከትላንት በስቲያ ዩናይትዶች ማንም ባልጠበቀው መልኩ በአማድ ዲያሎ ተአምር እና ተፆእኖ ፈጣሪነት ከኤቲሀድ በጨዋታው መጠናቀቂያ ሽርፍራፊ ሰከንዶች አከታትለው ባስቆጠሯቸው ጎሎች 2-1 በሆነ ውጤት በማስመዝገብ ሲቲ ላይ ጣፋጭ ድል ማስመዝገባቸው የሚታወቅ ነው።
ታዲያ ከጨዋታው በፊት ማርከስ ራሽፈርድ እና አሌሀንድሮ ጋርናቾ ከተጓዡ የማንቸስተር ዩናይትድ ስብስብ በአሰልጣኙ ሩበን አሞሪም ስር ውጪ መደረጋቸው አይዘነጋም። ውሳኔው ያልተገመተ ፤ ያልታሰበ እና መነጋገሪያ ነበር ፤ ግን በቀድሞ አንጋፋ የቡድኑ ተጫዋቾች ማለትም ጋሪ ኔቭልን ጨምሮ በዴቪድ ቤካም የተወደሰ እና የተደነቀ ውሳኔን አሞሪም ስለመወሰኑ ተናግረዋል።
እንደ Manchester evening news ዘገባ ከሆነ በሁሉም ጨዋታዎች የማንቸስተር ዩናይትድ ኮኮብ ጎል አስቆጣሪ የሆነው አሌሀንድሮ ጋርናቾ ከስብስቡ የተቀነሰበት ውሳኔ ከወንድሙ ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል። ለቡድኑ ዝግጅት እጅግ ቁልፍ የሆነውን ጉዳይ ጨዋታ ከመጀመሩ ከ24 ሰአት በፊት ሾልኮ መውጣቱ ማለትም የቡድኑን ቋሚ 11 ቀደም ብሎ በማህበራዊ ትስስር ገፆች በጋርናቾ ወንድም ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ይሄንን ነገር መቆጣጠር ያለበት እና መረጃውንም የሚያደሰው ጋርናቾ ስለሆነ ቅጣት እንዲሆነው በማሰብ ነው በሩበን አሞሪም በስብስቡ ውጪ እንዲሆን የተደረገው።
አሞሪም ሁሉንም ነገር መቆጣጠር ለኛ ከባድ ነው። ክለቡ ትልቅ ነው ፤ ብዙ አይን እና ጆሮ አሉት ፤ ተጫዋቾች ከወኪሎቻቸው ፤ ከወዳጆቻቸው ጋር ሊያወሩ ይችላሉ ግን ተቀባይነት የለውም ፤ ለኛ ጥሩ አይደለም እስቲ በቀጣይ ጨዋታ ቋሚ 11 አይን ቀድሞ ከሾለከ እናያለን ሲል ሀሳብ ሰጥቶበታል።
ከራሽፈርድ ጋር በተያያዘ የተቀመጠለት Standard አለ ፤ ያንን ግብ ማሳካት አለበት ብዙ ተጫዋቾች ቋሚ 11 ውስጥ መግባት ይፈልጋሉ ስለዚል ፉክክር አለ ራሽፈርድም ሆነ ጋርናቾ ጥሩ አቅም አላቸው እና ቦታቸውን ለማስጠበቅ ጥረት ያደርጋሉ ብዬ እጠብቃለሁ ሲል ነገሮችን አስረግጦ መስመር አሲዞ ተናግሯል። ራሽፈርድ ከ40-45 ሚሊዮን ፓውንድ ተለጥፎበት ለገበያ የወጣ ተጫዋች ስለመሆኑ እየተገለፀ ይገኛል።
ታዲያ በበርካቶች የቴን ኸግ እና የጄደን ሳንቾ ፤ የልዊ ቫን ሀል እና የአንሄል ዲማሪያ ፤ የጆዜ ሞሪንሆ እና የፖል ፖግባ ጉዳይ አሁን በአሞሪም እና ራሽፈርድ ልንመለከት ነው የሚል ሀሳብ እየሰጡ ይገኛሉ። ጋሪ ኔቭል እና ዴቪድ ቤካም ግን It’s the beginning of cultural reform ወይም የቡድኑ ጥልቅ ተሀድሶ መነሻ ጉዳይ እና ማሳያ ድርጊት ነው የሚበረታታ ነው ሲሉ ሀሳብ ሰጥተዋል።
ማንቸስተር ዩናይትዶች በቀጣይ በካራባኦ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ የፊታችን ሀሙስ ከቶተንሀም ጋር የሚገናኙ ይሆናል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ