👉ቦሌ አራብሳ የጋራ መኖሪያ ቤት የደረሳቸዉ ቅሬታ አቅራቢዎች በበኩላችዉ ግቡ ተብሎ ቀነ ገደብ ቢቀመጥም ምንም የተሟላ መሰረተ ልማት የለም ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ታኅሳስ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ ጊዜያት በዕጣ እና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪው ያልገባባቸው የጋራ መኖርያ ቤቶች የቤት ባለቤቶቹ እንዲገቡባቸው የተሰጠው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ዕጣ የወጣላቸው የቤት ባለቤቶች በጋራ መኖሪያዎቹ ውስጥ ለመግባት አለመቻላቸውንና መሰረተ ልማቶች ያልተሟሉባቸዉ አከባቢዎች መኖራቸዉን ለመናኸሪያ ሬዲዮ ቅሬታ አቅርበዋል።
ቦሌ አራብሳ አካባቢ ብሎክ 21 የቤት ባለ ዕጣ የሆኑት ቅሬታ አቅራቢ እንደገለፁት ፤ የተሰጠን ቤት መሰረተ ልማት ተብለዉ የሚጠቀሱ ነገሮችን አላሟላም ብለዋል፡፡ በተለይም ዋና ዋና የሚባሉት መጸዳጃና ውሃ እንዲሁም ኤሌክትሪክ ባልተሟላበት ሁኔታ ነው እንድንገባ የተወሰነዉ የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዋ አክለውም የየክፍሎቹ በሮችን ጨምሮ ሌሎች መሰረተ ልማቶች በግል ለማሟላት አቅማችን አይፈቅድም እናሟላ ቢባል እንኳን የመንገዱ ሁኔታ ለትራንስፖርት ምቹ ባለመሆኑ ተቸግረናል ሲሉም ሃሳባቸዉን ገልጸዋል፡፡
የቀረበውን ቅሬታ ተከትሎ መናኸሪያ ሬዲዮ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የኮንስትራክሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ፍቃዱ አለሙን አነጋግሯል ። መሰረተ ልማት ያልተሟላላቸው ብለን ከያዝናቸው ውስጥ ቦሌ አያት ሁለት እና አራብሳ ነበሩ አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ውሃና ኤሌክትሪክ ሃይልን ጨምሮ የመሰረተ ልማቶችን አሟልተናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የመንገድ ዝርጋታውን በተመለከተም ከሞላ ጎደል የተጠናቀቀ መሆኑን አመላክተው ፤ በተለይም ውሃ በየብሎኩ ከማቅረብ በተጨማሪ አንዳንድ መቆራረጥ ያለባቸው ቦታዎች ላይ ሌሎች አማራጮች መዘርጋታቸውንና አሁን ላይ ባለዕድለኞች ያልገቡባቸውን ቤቶች በኮሪደር ልማቱ የተነሱ ባለ ዕጣዎች እየገቡባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ ጊዜያት በዕጣ እና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪው ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቤት ባለቤቶቹ እንዲገቡባቸው በተሰጠው ጊዜ ካልገቡ በህግ አግባብ ውል የሚያቋርጥ መሆኑን መግለፁ የሚታወስ ነው ።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ