ታኅሳስ 08 ቀን 2017 ዓ.ም(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ የአስራ አንድ ዓመት ሕፃን ልጅ በማገት ወደ ሸገር ከተማ በማምጣት 4 ሚሊዮን ብር የጠየቀውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ተገልጿል፡፡
አጋች አበራ አላዩ ቸርነት ከሚኖርበት ሸገር ከተማ በመነሳት አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ዎኮ ፍቅረ ሰላም ቀበሌ ከሚኖር ገብረመድህን አላዩ ቸርነት ከተባለ ወንድሙ ጋር በመሆን ህዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 4:30 ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ የሚገኘውን የአቶ አውሌ ገብሩ ሀብተሚካኤል መኖሪያ ቤትን ሰብረው በመግባት ጥይት ተኩሰው በማስፈራራት የታጋቹን እናትና እህቶቹን እጅ በገመድ ወደኋላ የፍጥኝ በማሰር ሕፃን ባሳዝነው አውሌ ገብሩን አግተው ለሦስት ቀናት ዋሻ ውስጥ በማሳደር ሕፃኑን ይዘው በእግር እስከ ፍቼ ከተጓዙ በኋላ ሁለተኛው አጋች ገብረመድህን አላዩ ቸርነት ወደ አማራ ክልል ተመልሷል ነው የተባለው፡፡
አጋቹ አበራ አላዩ ቸርነት ሕፃኑን ህመምተኛ በማስመሰል በብርድ ልብስ በመሸፈን በሕዝብ ትራንስፖርት ከፍቼ ከተማ ወደ ሸገር ከተማ ቡራዩ ክ/ከተማ በማድረስ በተከራየው መኖሪያ ቤት ውስጥ በመደበቅ ለሕፃኑ አባት ለአቶ አውሌ ገብሩ ሀብተሚካኤል ስልክ በመደወል 4 ሚሊዮን ብር እንዲከፍል ይህ ካልሆነ ግን ሕፃኑን በሕይወት እንደማያገኘው በማስፈራራት ላይ እንዳለ ጉዳዩን የሰማው አዲስ አበባ ከተማ የሚኖረው የሕፃኑ አጎት ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ EFPApp ሞባይል መተግበሪያ ያደረሰውን መረጃ መነሻ በማድረግ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም አጋቹን በተከራየው መኖሪያ ቤት ውስጥ ከተባባሪ ባለቤቱ ጋር እጅ ከፍንጅ በመያዝ በቁጥጥር ስር አውሎ የሕፃኑን ሕይወት መታደግ መቻሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መመሪያም በአጋቾቹ ላይ ምርመራ እንደሚጀምርም ተመላክቷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ